የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 05/2013
የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
- ምድብ-1፡ office Furnitures
- ምድብ -2: Computers, Video camera and other Office Electronics Equipment
- ምድብ-3፡ Refrigerators; Water Dispenser & Coffee Machine
ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መመዘኛዎች ማሟላት የሚችሉ ድርጅቶች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በጨረታው ለመካፈል ተጫራቶች አግባብነት ያለው የዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስክር ወረቀት (VAT)፤ የግብር ክፍያ መለያ የምስክር ወረቀት (TIN) ፤ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ባወጣው የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀትና ጨረታ ላይ እንዲሳተፉ ከግብርና ታክስ ሰብሳቢ መ/ቤቶች የሚሰጣቸውን የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለምድብ–ብር 10,000.00፧ ለምድብ-2 ብር 25,000.00 እና ለምድብ-3 ብር 10,000.00 የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ( CPO ) ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ምድብ የቴክኒክ እና የፋይናንስየመወዳደሪያ/የመጫረቻ ሰነዶች በተለያዩ ሁለት በታሸገ ኤንቨሎፖች በአንድ ኦሪጂናልና በአንድ ኮፒ እስከ 4/2/2013 ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ድረስ በድርጅቱ የስብሰባ አዳራሽ ቢሮ ቁጥር 602 ለዚህ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በዚሁ ቀን በ4/2/2013 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓትተዘግቶ በዚያው ዕለት በ4፡05 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በቢሮ ቁጥር 602 ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ምድብ የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር ) በመክፈል ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን አንስቶ ከድርጅቱ ግዥና ትራንስፖርት ክፍል ቢሮ ቁጥር 006 መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡– ሜክሲኮ አደባባይ ወደ ሣርቤት በሚወስደው መንገድ 300 ሜትር ዝቅ ብሎ፡፡
ስልክ ቁጥር 011-551-32 88 ፖሣቁ 3375 አአ
የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ
ድርጅት