የግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ብዝሃ ህይወት ኢንስቲትዩት ግንባታው ያልተጠናቀቀ የፍቼ ጂን ባንክ ከነእቃው ለማስገንባት በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ ጋብዞ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም:
- የደረጃ 4 እና በላይ የግንባታ ፈቃድ ያላችሁ፣
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው፣
- ህጋዊ የዘመኑ የታደሰ የሥራ ፈቃድ ያለው፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ፣
- የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣
- የገቢዎች የመጫረት መብት ፈቃድ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል፣
- በመንግስት የግዥ ኤጀንሲ የአቅራቢዎች ዝርዝር ምዝገባ ማስረጃ የሚያቀርብ፣
- የመልካም ስራ አፈፃፀም ሊያቀርብ የሚችል፣ (ከ3 ዓመት ወደዚህ ያለ ቢያቀርብ ይመረጣል)
- ተጫራቹ የሚያቀርበው ዋጋ ቫትን የሚያካትት ለመሆኑ በሰነዱ ላይ በግልጽ ማመልከት ይኖርበታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ብር 100 (አንድ መቶ) በመክፈል ከኢንስቲትዩቱ ቢሮ ቁጥር 13 መውሰድ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር ) በባንክ በተረጋገጠ ቦንድ ፣ ቼክ (CPO) ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር የግድ አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸሁን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ቴክኒካል ሰነድ፦ ኦርጅናልና ኮፒ፣ፋይናንሻያል ሰነድ : ኦርጅናልና ኮፒ ለይቶ በማሸግ እንደገና ደግሞ ቴክኒካሉን ብቻውን ፋይናንሻያሉን ብቻውን አሽጋችሁ በሰነዱ ላይ ስም፣ ሙሉ አድራሻ፣ ፊርማችሁንና ህጋዊ ማህተማችሁን ማስቀመጥ አለባችሁ፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በወጣ ተከታታይ በ21ኛው ቀን ከሰዓት 8፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዛው ቀን 9፡00 ሰዓት በኢንስቲትዩቱ ግዥ ክፍል ( አዳራሽ ) ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል :: ሆኖም ግን የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በዚሁ ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል፡፡
- ኢንስቲትዩቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- የኢትዮጵያ ብዝሀ ህይወት ኢንስቲትዩት ኬኒያ ኤምባሲ ጎን ነው፡፡
ተጨማሪ ማስረጃ ቢፈልጉ በስልክ ቁጥር 011-661-66-43 /011-661-53-69 በመደወል ማብራሪያ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የኢትዮጵያ ብዝሃ ህይወት ኢንስቲትዩት