የሥራ ጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ከሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በህፃናት ላይ የሚሰሩ የሬድዮ እና የቴሌቭዥን ፕሮግራሞች ደረጃቸውን በጠበቀና ወጥ በሆነ መልኩ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ የሚያስችል የአሰራር ስርዓት ለመዘርጋት በሐገር አቀፍ ደረጃ ጥናት ለማስጠናት ይህን የሥራ ጨረታ አዘጋጅቷል። ይህ የስራ ማስታወቂያም በዘርፉ የተለያዩ የጥናት ሰነዶችን ያዘጋጀና ብቃት ያላቸው ድርጅቶች በህጻናት ሁለንተናዊ እድገትና ጥበቃ (Child Development & Protection) ላይ እንዲሁም የቤተሰብ ክህሎትና እውቀት ፣ ህጻናትን በተመለከተ በብዙኃን መገናኛዎች የሚተላለፉ ፕሮግራሞች ይዘት (Content)፣ መጠንና ሽፋን በልዩ ጥንቃቄና ትኩረት ወጥነት ባለው መልኩ የጥናት ጽሁፎች ላይ የተሰማሩ ድርጅቶችን በይፋ አወዳደሮ ለመቅጠር የወጣ ነው።
አላማ
- የህፃናትን ጉዳይ በሁሉም የሬድዮ እና የቴሌቭዥን አውታሮች የቅድሚያ አጀንዳ ሆኖ ትርጉም ባለው መልኩ የሚተገበርበትን አሰራር በመዘርጋት ሁለንተናዊ ደህንነቱ የተጠበቀ መልካም ትውልድ ማፍራትና ጥቅም ላይ የሚውሉ የሚዲያ መልክቶች ይዘት ለሚከተሉት ጉዳዮች ትኩረትና አጽዕኖት በሰጠ አግባብ ማዘጋጀት ይጠበቅባቸዋል፡
- በህፃናት ሁለንተናዊ እድገት የግንባታ ሂደት የብዙሀን መገናኛዎችን ሚና ማሳደግ፣
- ህፃናትን በተመለከተ በብዙሀን መገናኛዎች የሚተላለፉ ጉዳዮች ይዘት ማሻሻል፣
- ሁሉም የብዙሀን መገናኛዎች በትውልድ ግንባታ ሂደት የሚመሩበትን አሰራር መዘርጋት፣
ተወዳዳሪ ድርጅቶች ማሟላት/ማቅረብ የሚገባቸው ቅድመ ሁኔታዎች/ጉዳዮች
- ምክረ–ሃሳባቸውን በአማርኛ ወይም በእንግሊዝኛ ቋንቋ አዘጋጅተው ማቅረብ ይችላሉ:: ስለሚያዘጋጁት ሠነድ መቼ፣ እንዴት፣ በማን እንደሚተገብሩት ከሚገልጽ የድርጊት መርሃ ግብር እና ሥራውን በምን ያህል ገንዘብ እንደሚያከናዉኑት ከሚገልጽ የዋጋ መግለጫ ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- የድርጊት መርሃ–ግብሩ እና የዋጋ መግለጫውን በተለያየ ፖስታ አሽገው ማስረከብ የሚጠበቅባቸው ሲሆን በአንድ ፖስታ ታሽገው የሚቀርቡ መወዳደሪያ የቴክኒክ ምክረ–ሃሳብ እና የዋጋ መግለጫ ሰነዶች ከውድድር ውጪ ይደረጋሉ።
- ተወዳዳሪዎች የታደሰ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና ቲን ቁጥር ምዝገባ፣የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ማስረጃ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው::
- CPO/cash Payment order/ የ50000 ብር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው። በተጨማሪም የአቅራቢነት ምዝገባ ቢቀርብ የተሻለ ነው::
በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎቱ ያላቸው በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶች ምክረ–ሃሳባቸውን እና የዋጋ መግለጫ ሰነዳቸውን ይህ የስራ ጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉ ተከታታይ 15 የሥራ ቀናት ውስጥ ባለሥልጣኑ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማስገባት መሳተፍ ይችላሉ።
ባለስልጣኑ የስራ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ተጨማሪ መረጃ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 0912085683 ወይም 0912492984 ደውሎ ማግኘት ይቻላል።
Ethiopian Broadcasting Authority office
Phone: 0115573362
አድራሻ፡– የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን
አዲስ አበባ ፡– ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ኦሎምፒያ ከኤግዚቢሽን ማእከል ጀርባ