የብሔራዊ ካፌ አገልግሎት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር የሠራተኞች መረዳጃ ዕድር ክበብ የሠራተኛውን መዝናኛ ክበብ አገልግሎት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማከራየት ይፈልጋል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር የሠራተኞች መረዳጃ ዕድር ክበብ የሠራተኛውን መዝናኛ ክበብ አገልግሎት በግልፅ ጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች ከ8/3/2013 ዓ ም ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ጠቅላላ አገልግሎት ክፍል ቢሮ ቁጥር ቀርበው የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 50.00 /ሃምሣ ብር ከፍለው መውሰድ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡ ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው እስከ 24/3/2013 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ድረስ በቴአትር ቤቱ ጠቅላላ አገልግሎት ክፍል ማስገባት ይችላል፡፡
ጨረታው 24/3/2013 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ይዘጋና ወዲያውኑ በ9፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ለጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና የሚከፈልና የጨረታው ውጤት ከታወቀ በኋላ ወዲያውኑ የሚመለስ ብር 3000.00 /ሶስት ሺህ ብር/ በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር የሠራተኛ መረዳጃ ዕድር ከበቡ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 09 13 05 35 72 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር