የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር 03/2012 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር በ2012 በጀት አመት ሳውንድ ሲስተም በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
ስለሆነም፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ በገ/ኢ/ል/ሚ/ር የእቃና አገልግሎት አቅራቢነት ሊስት ዌብ ሳይት የተመዘገቡበትን ምስክር ወረቀት ፤የዘመኑን አግባብነት ያለው የታደሰ ንግድ ፍቃድ ፤ተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ፤የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው::
- ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የሚያሳይ የጨረታ ሰነድና የተጫራቾችን መመሪያ ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 100.00/አንድ መቶ ብር/ በመክፈል በብሔራዊ ቴአትር ቢሮ ቁጥር 13 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ አድርገው ሙሉ አድራሻቸውን ክ/ከ/ ወረዳ ፤ ቤት”ቁጥር ፤ስልክ ቁጥራቸውን በመጻፍ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከቀኑ በ8፡00 ድረስ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00/አስር ሺህ ብር/ ከታወቀ ባንክ በሚሰጥ የተረጋገጠ ቼክ ወይም (CPO) የጨረታ መክፈቻ ቀን ከመድረሱ በፊት ከጨረታ ሠነዳቸው ጋር በማያያዝ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው::
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን ከቀኑ በ8፡30 በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ቢሮ ቁጥር 13 ይከፈታል ትክክለኛው ቀን የጨረታ ሰነዱ ላይ የሚገለፅ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- የእቃው ርክክብ የሚፈጸመው በብሔራዊ ቴአትር ንብረት ክፍል ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው፡፡
አድራሻ፡– ቂርቆስ ክ/ከ ወረዳ 7
ለተጨማሪ ማስረጃ ፡– 0115513735 እና 0115158244 መጠየቅ ይቻላል
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር