የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ማህበር
ተሸከርካሪዎችን (Automobiles) ለመግዛት የወጣ
የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ቤተስብ መምሪያ ማህበር በበጎ ፈቃደኞች ተሳትፎ የተመሰረተ ለትርፍ ያልተቋቋመ አገር በቀል መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ነው። የተቋቋመበት ተልእኮም ተጋላጭ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች በተለይም የእናቶችንና ህፃንትን ጤንነትን ለመጠበቅ እንዲሁም ሴቶችና ወጣቶች ጥራቱን የጠበቀ እና ሁሉን አቀፍ የሆነ አማራጭ የተዋልዶ ጤና አገልግሎት እንዲያኙ ማስቻል ነው፡፡
የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ማህበር ለማህበረሰቡ የሚሠጠውን አገልግሎት ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ እንዲችል የሚያገለግሉና ከዚህ በታች በስንጠረዥ ውስጥ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች (እስፔሲፊኬሽንስ) በሚያሟላ መልኩ አነስተኛ መኪናዎችን (Automobiles)ማቅረብ የሚችሉ ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ተ.ቁ |
ብዛት |
መግለጫ |
1 |
2 |
Automobile Zero Mile (Brand New) 4 speed transmission or above 1400 CC displacement or above Fuel type Petrol and Fuel tank Capacity 40 litter and above Seating capacity 5 seater Ground clearance 150 mm and above: |
በመሆኑም፣
- የአመቱን የመንግስት ግብር የገበሩ እና በዘርፉ ላይ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለው ፣
- የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ /የጨረታ ዋጋውን 1% በሲፒኦ ወይም በባንክ/ኢንሹራንስ ዋስትና ማቅረብ የሚችል፣
- የተሸከርካሪዎቹን ተጨማሪዝርዝር እስፔሲፊኬሽን እና የዋጋ ማቅረቢያውን መሳለኪያ አካባቢ መስከረም ማዞሪያ ወደ ውስጥ ገባ ብሎ ከሚገኘው ዋናው መስሪያ ቤት 3ኛ ፎቅ ሂሳብ ክፍል 309 በመገኘት የጨረታ ሠነዱን 100 ብር በመክፈል መግዛት የሚችል።
- ተጫራቾች ተሸከርካሪዎቹን የሚያቀርቡበትን ዋጋ፤ ህጋዊ የንግድ ሰነዶችን፤ የተሽከርካሪዎቹን የብቃት ማረጋገጫ ሰነዶች እና ሌሎች ሰርተፍኬቶችን እንዲሁም የተሸከርካሪዎቹን ዝርዝር እስፔሲፊኬሽን የሚያሳዩ ፍላየሮች /ማኑዋሎች፣ ወይም ፎቶዎች እንዲሁም ሌሎች አጋዥ ሰነዶችን ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ የአማርኛው እትም ከወጣበት ቀን አንስቶ እስከ ረቡእ ጥቅምት 18 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 6፡30 ሰዓት ድረስ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦርጂናልና አንድ ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በእለቱ ጥቅምት 18 ቀን 2013 ዓ.ም ከሰኣት ቡሃላ በ8፡00 ሰዓት በጨረታው ለመገኘት በፈቀዱና እና መገኘት በቻሉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ፊት ይከፈታል፡፡
- ማህበሩ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ ወይም የሚገዛውን መጠን የመቀየር መብቱ የተጠበቀ ነው::
አድራሻ፡
የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ማህበር ዋናው መ/ቤት
ደብረዘይት መንገድ፣ መስከረም ማዞሪያ፣ ሪቼ አካባቢ
(በቅሎቤት)
ስልክ : +251 114 672300
Fax: +251 114 671084