የጨረታ ማስታወቂያ
የማስታወቂያ ቁጥር ብ/ግ/ጨ /01/2013
የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን በዋናው መ/ቤት የሕንፃ ግራውንድ ውስጥ የሚጠራቀመውን ፍሳሽ ለማስወገድ በዘርፉ የተሰማሩትን በደረጃ 7 እና ከዚያ በላይ በGC፤ WC እና BC የሆናችሁትን በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡
በዚህ ጨረታ ላይ በመሳተፍ የምትፈልጉ ድርጅቶች
የሚከተሉትን ማሟላት አስባችሁ፡-
- በዘርፉ ለዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ፡፡
- የታክስ እና የግብር ግዴታቸውን የተወጡና የቲኢቲ ከፋይ፡፡
- የምዝገባ ሰርትፍኬት፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ወይም ጋራንቲ 300,000.00 (ሦስት ሺህ ብር)፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ከባለስልጣን መ/ቤቱ 9ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 903 መግዛት ይችላሉ፡፡
- ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ ቀኑ ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓል ላይ ከዋለ የጨረታ መክፈቻ ቀን በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ስዓት ይከፈታል፡፡
- ባለስልጣን መ/ቤቱ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ
ባለስልጣን