የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ቅርስ ባለአደራ
የጨረታ ቁጥር ኢቅባማ/ግጨ-03/2013
የቁም ባህር ዛፍ ሽያጭ ግልጽ ጨረታ
የኢትዮጵያ ቅርስ ባለአደራ ማኅበር ከሚያስተዳድራቸው በእንጦጦ የተፈጥሮ ፓርክ ውስጥ በሚገኝ ቦታ ስፋቱ 35.65 ሄክታር ላይ ያረፈ ለተለያየ አገልግሎት የሚውል የቁም ባህር ዛፎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ይህ ለሶስተኛ ጊዜ ለጨረታ የቀረበው ለተለያየ አገልግሎት የሚውል የቁም ባህር ዛፍ ካሉን አራት ክፍልፋ/ Compartment /በአንዱ ላይ ያለ ሲሆን ዝርዝር መረጃውም እንደሚከተለው ነው፡-
የምድብ መለያ ቁጥር |
የቁም ባህር ዛፍ ክፍልፋይ/ Compartment / |
መለኪያ |
የቁም ባህር ዛፍ የያዘው የመሬት ስፋት በሄክታር |
ቮሊዩም በሄክታር |
አጠቃላይ ቮሊዩም በሜትር ኩብ |
4 |
ሸዋ ርካብ የቁም ባህርዛፍ |
በጥቅል |
35.65 ሄ/ር |
38.7 ሜ.ኩ |
1379.6 ሜ.ኩ |
በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች:-
- የተዘጋጀውን የመጫረቻ ሰነድ በኢትዮጵያ ቅርስ ባለአደራ ማኅበር ቢሮ ቁጥር 2 በአካል በመቅረብ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ማግኘት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነድ ሽያጭ የሚካሄደው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ማለትም ከሰኞ እስከ ሐመስ ከጠዋቱ 3፡00 – 6፡30 እንዲሁም ከሰዓት ከ7፡ 30 – 11፡00 እና አርብ ከጠዋቱ 3፡00 – 5፡30 እንዲሁም ከሰዓት ከ7፡30 – 11፡00 ሰዓት ይሆናል
- ተጫራቾች ለመግዛት የሞሉትን ዋጋ 10 በመቶ (10%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ በኢትዮጵያ ቅርስ ባለአደራ ማኅበር ስም በማዘጋጀት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለመግዛት ያቀረቡትን የመግዣ ዋጋ በተያያዘው የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ ብቻ በመሙላት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከሚዘጋበት ቀንና ሰዓት ድረስ ባሉት የሥራ ቀናት በታሸገ ኢንቨሎፕ ለዚሁ ተብሎ በተጋጀው በጨረታ ሳጥን ውስጥ ከታች በተገለጸው አድራሻ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ሌሎች ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም፡፡
- አሽናፊ ተጫራች(ቾች) የጨረታ ውጤት ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 5/ አምስት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ከማኅበሩ ጋር ውል መፈራረም፣ የውል ማስከበሪያ ማቅረብና ባህር ዛፎቹን በአምስት ወራት ውስጥ በሚፈለገው ደረጃ ቆርጦ ማንሳት ይኖርበታል።
- የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን መስከረም 16 ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ4፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢትዮጵያ ቅርስ ባለአደራ ማኅበር መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ሆኖም የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓላት ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለጸው ሰዓት መሰረት ይሆናል፡፡
- ማኅበሩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡– ቦሌ መንገድ፣ ከቦሌ ማተሚያ ቤት ፊት ለፊት፣ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቦሌ ቅርንጫፍ በስተጀርባ፤ ከኢዮብ የድግስ ዕቃዎች ማከራያና የድንኳን ሥራ በስተ ቀኝ በኩል፤ በቀድሞ የራስ ከበደ መንገሻ ቤት – ቢሮ ቁጥር 2
ስልክ ቁጥር፡– ሞባይል 0911 65 12 06/ 09 11 64 12 53
የቀጥታ– 011 5 15 88 02
የኢትዮጵያ ቅርስ ባለአደራ ማኅበር