የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
ብ/ግ/ጨ/ESSTI/NCB/01/2013
የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የሰራተኛ ስርቪስ አገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሰረት
- ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የቫት ተመዘጋቢ እና ተፈላጊ ሰነዶች ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ሰነድ ግዢ ሲመጡ የማይመለስ ብር 100 በመክፈል በኢንስቲትዩቱ ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ድረስ በመምጣት ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በCPOወይም በጥሬ ገንዘብማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
ሎት ቁጥር |
የሚፈፀመው ግዥ |
የጨረታ ማስከበሪያ |
መግለጫ |
1 |
የሰራተኛ ሰርቪስ አገልግሎት ግዥ |
ብር 5,000 |
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ |
4. ማንኛውም ተጫራች የመወዳደሪያ የጨረታ ሰነዱን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ ማቅረብ የሚኖርበት ሲሆን ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት በኢንስቲትዩቱ የግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለበት፡፡
5. የጨረታ መክፈቻ ቀን ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ከ15ተከታታይ ቀናት በኋላ ባለው መጀመሪያ የስራ ቀን ከሰዓት በኋላ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ ወዲያውኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል:: የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል
6. ተጫራቾች በጨረታው ለመወዳደር በአቅራቢዎች ዝርዝር መመዝገባቸውን የሚያሳይ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
7. ኢንስቲትዩቱ ጨረታውን እንደአስፈላጊነቱ በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
አድራሻ፡-
አዲስ አበባ ጉለሌ ወረዳ2፣ የቤት ቁጥር 179
የስልክ ቁጥር፡-011-872-0257
ምስካየ ኅዙናን ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት ወደ መነን
በሚወስደው መንገድ በሚገኘው ህንፃ
በኢፌዲሪ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ
ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ
ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት