የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት ለፋሲሊቲ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የምግብ ግብዓቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለዓመት ውል በመያዝ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም
የሎት ቁጥር |
የምግብ ግብዓቱ ዓይነት |
የሎት ቁጥር |
የምግብ ግብዓቱ ዓይነት |
ሎት – 1 |
ወተትና የወተት ውጤቶች |
ሎት -6 |
ጥራጥሬ እና የጥራጥሬ ውጤቶች ፤ |
ሎት -2 |
የዶሮ ስጋ እና እንቁላል |
ሎት-7 |
አትክልትና ፍራፍሬ |
ሎት -3 |
የበሬና በግ ስጋ |
ሎት-8 |
የታሸጉ እና ፕሮሰስ የሆኑ ምግቦች |
ሎት -4 |
የአሳ ስጋ |
ሎት-9 |
የታሸገ ውሃ/ከ 0.5-0.6 ሊ/ር/ |
ሎት -5 |
ቅመማ ቅመም |
|
|
ከላይ የተዘረዘሩትን ግብዓቶች ለማቅረብ የሚወዳደሩ ህጋዊ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸዉ፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ፤ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት ፤ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት፤ እና ሌሎች ተፈላጊ ሰነዶችን ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ከላይ የተዘረዘሩትን የምግብ ግብዓቶችን የሚያቀርቡበት ቦታ አዲስ አበባ እና ደ/ዘይት ስልጠና ማዕከል ቅጥር ግቢ ድረስ ይሆናል ፤
- ጨረታው በአየር ላይ የሚቆየው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ሲሆን ሰነዱ የሚሸጠው በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ዓርብ ከ2፡00-11፡00 የአንዱን ሎት የማይመለስ 100 ብር አዲስ አበባ በሚገኘው ዋናው ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 206 በጀትና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት በመክፈል ደረሰኝ ይዘው 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 406 የአቅርቦት እና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ በመምጣት ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ
- ጨረታው በአየር ላይ በዋለ በ15ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡
- የጨረታ ፖስታውን ፋይናንሺያል እና ቅድመ መገምገሚያዎቹን /ቴክኒካል ሰነድ/ በተለያየ ፖስታ ኦርጅናልና ኮፒ በማለት በፖስታ አሽጎ ማቅረብ አለበት፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን በሎት 5000.00/አምስት ሺህ ብር / በCPO ወይም ቢድ ቦንድ ብቻውን ወይም ከቴክኒካል/ህጋዊ ሰነዶች ጋር በፖስታ አሽጎ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል ::
- ኢንስቲትዩቱ ጨረታውን እንደአስፈላጊቱ በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ
አዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 ስልክ ቁጥር 0118-694931/0116-465554
ከሳህሊተ ምህረት ማርያም ቤ/ክርስቲያን ፊት ለፊት የሚገኘው ህንፃ
የኢትዮጵያ ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት