የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን /ኢሠማኮ ከLONORWAY እና Mondiaal ENV ከተባሉ ለጋሽ ድርጅቶች ጋር መተባበር በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ለተሠጠው ሥልጠና ማስፈፀሚያ በሥራ ላይ የዋለ የገንዘብ እንቅስቃሴ የሂሳብ ምርመራበታወቁ ኦዲተሮች በጨረታ አወዳድሮ ኦዲት ማስደረግ ይፈልጋል::
በዚህ መሰረት፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉና በሙያው የታደስ ሕጋዊ ፍቃድ ያላቸው
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር TIN/ ያላቸው፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ VAT/ ተመዝጋቢ የሆኑ፣
- በዋናው አዲተር መ/ቤት የተመዘገበና በመስኩ ሰርቲፋይድ የሆነበትን የሙያ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል
- ሂሳቡን የሚመረምርበት ዋጋና የሂሳብ ምርመራው የሚጠናቀቅበት ጊዜ በዝርዝር ማቅረብ የሚችል፣
- ተጫራቾች ከላይ በዝርዝር በተገለፀው መሰረት መሟላት የሚገባቸውን ሁሉ አሟልተው የጨረታ ሰነዱን በሰም በታሸገ ፖስታ ኢሠማኮ ግዥ ፣ ንብረትና ጠቅላላ አገልግሎት ክፍል ቢሮ ቁጥር 216 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 5 የስራ ቀናት ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል::
- ጨረታው ማስታወቂያው በወጣ በ6ኛው ቀን ከቀኑ በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል:: 6ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል::
- የሂሳብ ሰነዶቹን ኢሠማኮ ፋይናንስ መምሪያ በመቅረብ መመልከት ይቻላል፣
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን
ስልክ ቁጥር፡ 0115-15 49 57/0115-15 54 29