የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁ. ፋማዳ/ግሥአቡ/04/2013
የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ግዥዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ተ.ቁ |
የዕቃው ዓይነት |
ብዛት |
1 |
የፊት መሸፈኛ ማስክ (Face Mask) |
10,000 |
ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢዎች በጨረታው እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል፡፡
- በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና በመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ለመመዝገባቸው ከድረ–ገጹ (website) አትመው ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡና የግብር መለያ ሰርተፊኬት ያላቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አስባቸው፡፡
- ተጫራቾች የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለገሐር በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መሥሪያ ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 ድረስ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለምድብ አንድ ብር 10,000.00 (አስር ሺ) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ ክፍያ ማዘዣ (cpo) ወይም ለዘጠና ቀናት የሚቆይ ቅድመ ሁኔታ ያላስቀመጠ የባንክ ዋስትና ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው::
- ተጫራቾች መወዳደሪያ ሠነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ለገሐር በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ነሐሴ 22 ቀን 2012 ዓ.ም እስከ ቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዕለቱ ማለትም ነሐሴ 22 ቀን 2012 ዓ.ም በፋሲሊቲ ማኔጅመንት የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፤
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡– 011-5512400 የውስጥ መስመር 217 ወይም በቀጥታ 0115504931 መጠየቅ ይቻላል
የኢትዮጵያ መድን ድርጅት