የቤት ኪራይ የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ መድን ድርጅት አዲስ አበባ ከተማ ለገሃር አካባቢ በሚገኘው ዋ/መ/ቤት ሕንጻ ምድር ወለል ላይ የሚገኙትን ሁለት ክፍሎች ለንግድ አገልግሎት በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡
- በጨረታ መወዳደር መሣተፍ የሚፈልግ ድርጅት ወይም ግለሰብ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት ከሰዓት በኋላ ከ7፡00 ሰዓት እስከ 9፡30 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት እስከ 5፡30 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመክፈል ለገሃር አካባቢ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ፋሲሊቲ ማኔጅመንት ዋና መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 107 በመገኘት የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ክፍል የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5000.00 (አምስት ሺ ብር) በባንክ ማዘዣ ክፍያ (CPO) ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጥቅምት 16 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዶቻቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በድርጅቱ ዋና መ/ቤት ፋሲሊቲ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 107 ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ጨረታው ጥቅምት 16 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሰነዱ በድርጅቱ ዋና መ/ቤት ፋሲሊቲ ማኔጅመንት መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡-0115517075- አዲስ አበባ
የኢትዮጵያ መድን ድርጅት