ብሄራዊ ግልጽ ጨረታ
የጨረታ መለያ ቁጥር፡ መአኤ/04/2013
የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ Automatic Document Feeder (ADF) Duplex color scanning Machine በዘርፉ ከተሰማሩ እና ህጋዊ ከሆኑ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ::
- ሀ. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ለ. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ሐ .በመንግስት ግዥ ለመሳተፍ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ መ. ከሀገር ውስጥ ገቢ ባለስልጣን ታክስ ክሊራንስ (ጨረታው ከመከፈቱ በፊት የታደሰ) እና ሌሎች የህጋዊነት ሰነዶችን ማቅረብ የሚችሉ::
- ተጫራቾች መደበኛ የጨረታ ሰነዱን ከመድሃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ዋና መስሪያ ቤት ንብረትና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ግዥ ቡድን ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ተመላሽ የሚሆን በ/ETHIOPIAN Pharmaceutical SUPPLY AGENCY/ ስም የተሰራ ስሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ብር 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ ብር) ማስያዝ አለባቸው
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን እስከ ጥቅምት 11/2013 ዓ.ም ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ማቅረብ አለባቸው::
- ጨረታው ጥቅምት 11/2013 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 8፡15 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ከጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት ውጭ የሚቀርቡ የመጫረቻ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም።
- ኤጀንሲው ጨረታውን በተመለከተ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡– ስልክ ቁጥር 011-2-76-52-94/011-2-78-30-08
ፖሳቁ-21904
የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ
ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል
ኮሌጅ ፊት ለፊት
አዲስ አበባ