የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር ቲ-10/2013
የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ከታች ስሎት የተገለፁትን ለመ/ቤቱ ተሽከርካሪዎች አገልግሎት የሚያስፈልጉ እቃዎችን በአገር ውስጥ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
- ሎት 1 የተለያዩ ተሽከርካሪዎች ጎማ
- ሎት 2 የተለያዩ ተሽከርካሪ ባትሪዎች
በጨረታው ለመሳተፍ ፍላጎት ያላቸው ነገር ግን በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ቀደም ሲል በድረገፅ ያልተመዘገቡ በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ዌብሳይት(ድረ ገጽ) ተመዝግበው የተመዘገቡበትን ማስረጃ በማያያዝ የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡ እቃዎቹ የሚቀርቡትና ሰመ/ቤቱ ቃሊቲ ቅርንጫፍ ግቢ ውስጥ በሚገኘው መጋዘን
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ከሚፈለገው አገልግሎት ጋር የተዛመደ የንግድ ስራ ፈቃድ፣የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን ማረጋገጫ ሰርተፍኬት እና በጨረታው ለመሳተፍ ከሀገር ውስጥ ገቢ ቢሮ የድጋፍ ደብዳቤ በማቅረብ የጨረታውን ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 ወይም በኢትዮጵያ ውስጥ ሊመነዘር በሚችል ተመጣጣኝ ሌላ ገንዘብ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቁጥር 1000002579859 በኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ስም በማስገባትና በባለስልጣኑ ዋና መ/ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 103 በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የሚወሰነው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተመለከቱት መስፈርቶች መሰረት ሲሆን ጨረታው ዜግነትን ሳይመለከት ለማንኛውም በዚህ ስራ ላይ ለተሰማራ ክፍት ነው፡፡የጨረታ ሰነዱ የተዘጋጀው በእንግሊዘኛ ቋንቋ ነው፡፡
- ተጫራቾች ጨረታቸውን ለዚህ ተግባር በተዘጋጀ ሳጥን ቢሮ ቁጥ 104 ገቢ የሚያደርጉበት የመጨረሻ ቀን ህዳር 18 ቀን 2013 ዓ.ም እስከ ጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ነው፡፡
- ተጫራቾች ለሎት 1 ከብር 300,000.00 (ሶስት መቶ ሺ) ያላነሰ ሎት 2 ከብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺ) ያላነሰ ወይም በኢትዮጵያ ውስጥ ለመነዘር በሚችል ተመጣጣኝ ሌላ ገንዘብ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ርክ በጥሬ ገንህ ብ ወይም በባንክ ዋስትና ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከዚህ ውጭ በኢንሹራንስ ወይም በሌላ መልክ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም።
- ጨረታው ተጫራቹ ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ህዳር 18 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት በዋናው መ/ቤት የቀድሞው ህንፃ በሚገኘው አዲሱ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- ተጫራች በጨረታው ደንብና መመሪያ መሰረት ጨረታቸውን ማቅረብ አለባቸው፡ከጨረታው ደንብና መመሪያ ውጭ የሚቀርብ ማንኛውም ጨረታ ተቀባይነት የለውም፡፡
- መ/ ቤቱ ስለ ዕቃዎቹ ግዥ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፈል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ ተጫራች የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ፡፡
የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን
ፓስታ ሳጥን ቁጥር 1770
ስልክ ቁጥር +251151534 41 ወይም +251115530423
ሜክሲኮ ዋቢ ሸበሌ ሆቴል ፊት በፊት
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
የኢትዮጵያ መንገዶች ባስስልጣን