Construction Machinery / Construction Machinery and Equipment / Machinery and Equipment / Others / Vehicle

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን በስሩ ለሚገኙት የመንገድ ጥገና ዲስትሪክቶች (አዲግራት፣ እለምገና ፣ ኮምቦልቻ ፣ ደብረማርቆስ ፣ ድሬደዋ፣ ጎንደር፣ ጅማ፣ ነቀምት፣ ሻሸመኔ እና ሶዶ) ላይ ለሚያከናውናቸው የጥገና ስራዎች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎችን (ዳምፕ ትራክ፣ዶዘር፣ግሬደር፣ ኤክስካቫተር ባለ ጃክ ሀመር፣ኤክስካቫተር ባለ ጎማ ፣ የውሀ ቦቴ ተሸካሚ ተሽከርካሪ፣ ሎደር፣ ቼይን ኤክስካቫተር እና ሮለር) በአገር ውስጥ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል

የኪራይ ጨረታ ማስታወቂያ 

ቁጥር ቲ-01/2013 

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን በስሩ ለሚገኙት የመንገድ ጥገና ዲስትሪክቶች (አዲግራት፣ እለምገና፣ ኮምቦልቻ፣ ደብረማርቆስ፣ ድሬደዋ፣ ጎንደር፣ ጅማ፣ ነቀምት፣ ሻሸመኔ እና ሶዶ) ላይ ለሚያከናውናቸው የጥገና ስራዎች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎችን (ዳምፕ ትራክ፣ዶዘር፣ግሬደር፣ ኤክስካቫተር ባለ ጃክ ሀመር፣ኤክስካቫተር ባለ ጎማ፣ የውሀ ቦቴ ተሸካሚ ተሽከርካሪ፣ ሎደር፣ ቼይን ኤክስካቫተር እና ሮለር) በአገር ውስጥ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል፡፡በጨረታው ለመሳተፍ ፍላጎት ያላቸው ነገር ግን በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ቀደም ሲል በድረገፅ ያልተመዘገቡ በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ዌብሳይት(ድረ ገጽ) ተመዝግበው የተመዘገቡበትን ማስረጃ ስማያያዝ የኪራይ ጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡ እቃዎቹ የሚቀርቡት ከላይ በተገለፁት የመ/ቤቱ ቅርንጫፍ ውስጥ ነው፡፡ 

  1. ተጫራቶች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ከሚፈለገው አገልግሎት ጋር የተዛመደ የንግድ ስራ ፈቃድ፣የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን ማረጋገጫ ሰርተፍኬት እና በጨረታው ለመሳተፍ ከሀገር ውስጥ ገቢ ቢሮ የድጋፍ ደብዳቤ በማቅረብ የጨረታውን ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 ወይም በኢትዮጵያ ውስጥ ሊመነዘር በሚችል ተመጣጣኝ ሌላ ገንዘብ በመክፈል በባለስልጣኑ ዋና መ/ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 103 በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ መግዛት ይችላሉ፡፡ 
  2. የጨረታው አሸናፊ የሚወሰነው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተመለከቱት መስፈርቶች መሰረት ሲሆን ጨረታው ዜግነትን ሳይመለከት ለማንኛውም በዚህ ስራ ላይ ለተሰማራ ክፍት ነው፡፡ የጨረታ ሰነዱ የተዘጋጀው በእንግሊዘኛ ቋንቋ ነው፡፡ 
  3. ተጫራቾች ጨረታቸውን ለዚህ ተግባር በተዘጋጀ ሳጥን ቢሮ ቁጥር 103 ገቢ የሚያደርጉበት የመጨረሻ ቀን ነሐሴ 8 ቀን 2012 ዓ.ም እስከ ጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ነው፡፡ 
  4. ተጫራቾች ከብር 10,000.00 (አስር ሺ ብር) ያላነሰ ወይም በኢትዮጵያ ውስጥ ሊመነዘር በሚችል ተመጣጣኝ ሌላ ገንዘብ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ቼከ፣በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ ዋስትና ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከዚህ ውጭ በኢንሹራንስ ወይም በሌላ መልክ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም፡፡ 
  5. ጨረታው ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ነሐሴ 08 ቀን 2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት በዋናው መ/ቤት በሚገኘው አዲሱ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ 
  6. ተጫራቶች በጨረታው ደንብና መመሪያ መሰረት ጨረታቸውን ማቅረብ አለባቸው፡፡ ከጨረታው ደንብና መመሪያ ውጭ የሚቀርብ ማንኛውም ጨረታ ተቀባይነት የለውም፡፡ 
  7. መ/ቤቱ ስለ ዕቃዎቹ ግዥ የተሻለ መንገድ ካጊኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ 
  8. ለበለጠ መረጃ ተጫራቾች የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ፡፡ 

የኢትዮጵያ መንገዶች ባስስልጣን 

የእቃ ግዥ ቡድን 

ፓስታ ሳጥን ቁጥር 1770 

ስልክ ቁጥር +2511151534 41 ወይም +25111553 0423 

ፋክስ 0115507788 

አዲስ አበባ ኢትዮጵያ 

የኢትዮጵያ መንገዶች ባስስልጣን