የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር T-03/2012
የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ልዩ ልዩ ያገለገሉ የቢሮ መገልገያ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
- በባለሥልጣኑ ዋና መ/ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 104 በመቅረብ ይህ ማስታውቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የሚወሰነው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተመለከቱት መስፈርቶች መሠረት ሲሆን ጨረታው ዜግነትን ሳይመለከት ለማንኛውም በዚህ ሥራ ላይ ለተሰማራ ክፍት ነው፡፡ የጨረታ ሰነዱ የተዘጋጀው በአማርኛ ቋንቋ ነው፡፡
- ተጫራቾች ጨረታቸውን ለዚህ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ቢሮ ቁጥር 104 ገቢ የሚያደርጉበት የመጨረሻ ቀን ሰኔ 9 ቀን 2012 ዓ.ም እስከ ጥዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ነው፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሰኔ 9 ቀን 2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት በመ/ቤቱ 4ኛ ፎቅ በሚገኘው የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቶች በጨረታው ደንብና መመሪያ መሰረት ጨረታቸውን ማቅረብ አለባቸው፡፡ ከጨረታው ደንብና መመሪያ ውጭ የሚቀርብ ማንኛውም ጨረታ ተቀባይነት የለውም፡፡
- መ/ቤቱ ስለ ዕቃዎቹ ሽያጭ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- . ለበለጠ መረጃ ተጫራቾች የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ፡፡
የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን
የዕቃ ግዥና ቡድን የፖስታ ሣጥን ቁጥር 1770 የስልክ ቁጥር 0115530423 ወይም 0115517170
ፋክስ 01155077 88
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን