የብሔራዊ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር፡– ብግጨ/
ኢሕጤኢ/ግኬቲ/ የICTተዛማች
ዕቃዎች ግዢ/043/2012 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩ በ 2012 በጀት ዓመት የICT ተዛማች ዕቃዎች ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በዚህ ጨረታ ለመሣተፍ የሚፈልጉ፡-
- ተጫራቾች የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በጥሬ ገንዘብ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከኢንስቲትዩቱ ግዥ ኬዝ ቲም ቢሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት ከ2፡30 እስከ 6፡00 ሠዓት ከሰዓት በኋላ 7:30 -11፡00 ሰዓት መውሰድ ይችላሉ፣
- በግዥ ኤጀንሲ ዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ፣
- የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፣የዘመኑን ግብር የከፈሉና አግባብነት ያለው የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፣
- ታክስ ክሊራንስ (ከግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት የድጋፍ ደብዳቤ) የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት (TIN NO-)
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር ሎት አንድ 15,000 (አስራ አምስት ሺ ብር) እና ለሎት ሁለት 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በባንክ ዋስትና በማያያዝ እስከ ሰኔ 4/2012 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ግዥ ኬዝ ቲም ቢሮ ቁጥር 05 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ሆነው የተመረጡ ድርጅቶች የጨረታው ውጤት በደብዳቤ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ30 ቀናት ውስጥ በኢንስቲትዩቱ ግዥ ኬዝ ቲም በመቅረብ ያሸነፉበትን ዋጋ 10% ለመልካም ሥራ አፈፃፀም ዋስትና በማስያዝ ውል መፈረም አለባቸው::
- የጨረታው አሸናፊ የሆኑ ድርጅቶች በፈረሙት ውል መሠረት በራሳቸው ትራንስፖርት አሸናፊ የሆኑባቸውን የICT ተዛማች ዕቃዎች ኢንስቲትዩቱ ዕቃ ግምጃ ቤት ድረስ ማቅረብ አለባቸው::
- የጨረታው አሸናፊ ያልሆኑ ድርጅቶች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፒኦ የጨረታ አሸናፊው ተለይቶ የአሸናፊነት ደብዳቤ ከተሰጠው በኋላ ባሉት 5 ቀናት ውስጥ ይመለስላቸዋል፡፡
- የጨረታው ሳጥን ሰኔ 04/2012 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ይዘጋል ፡፡
- የጨረታው ሳጥን ሰኔ 04/2012ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲሁም የኢንስቲትዩቱ፡ ኦዲትና የስነ ምግባር ባለሙያ በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ከጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት በኋላ የሚቀርቡ የመጫረቻ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡
- ኢንስቲትዩቱ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩቱ
አድራሻ:- አርበኞች መንገድ ጳውሎስ ሆስፒታል አጠገብ
ስልክ ቁጥር፡-0112771054/56
ፋክስ፡-0112758634
የመ.ሣ.ቁ 1242/5456
አዲስ አበባ
የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና
ኢንስቲትዩት