የብሔራዊ ግልፅ
የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥው መለያ ቁጥር፡– ብግጨ/ኢሕጤኢ/ግኬቲ/ Data backup /050/2012 ዒም:: የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩቱ በ 2012 በጀት ዓመት የICT ተዛማች ዕቃዎች ግዢ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም በዚህ ጨረታ ለመሣተፍ የሚፍልጉ፡
- ተጫራቶች የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በጥሬ ገንዘብ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከኢንስቲትዩቱ ግዥ ኬዝ ቲም ቢሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት ከ2፡30 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት ከሰዓት በኋላ 7፡30 ሰዓት 11፡00 ሰዓት መውሰድ ይችላሉ::
- በግዥ ኤጀንሲ ዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ፤
- የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና አግባብነት ያለው የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡
ሐ. ታክስ ክሊራንስ (ከግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት የድጋፍ ደብዳቤ) የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት (TIN NO-)
4. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በባንክ ዋስትና በማያያዝ እስከ ግንቦት 14/2012 ዓም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ግዥ ኬዝ ቲም ቢሮ ቁጥር 05 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
5. የጨረታው አሸናፊ ሆነው የተመረጡ ድርጅቶች የጨረታው ውጤት በደብዳቤ ከተገለፀላቸው ቀንጀምሮ በoቀናት ውስጥ በኢንስቲትዩቱ ግዥ ኬዝ ቲም በመቅረብ ያሸነፉበትን ዋጋ 10% ለመልካም ሥራ አፈፃፀም ዋስትና በማስያዝ ውል መፈረም አለባቸው።
6. የጨረታው አሸናፊ የሆኑ ድርጅቶች በፈረሙት ውል መሠረት በራሳቸው ትራንስፖርት አሸናፊ የሆኑባቸውን ነገሮች ኢንስቲትዩቱ ዕቃ ግምጃ ቤት ድረስ ማቅረብ አለባቸው::
7. የጨረታውን አሸናፊ ያልሆኑ ድርጅቶች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፒኦ የጨረታ አሸናፊው ተለይቶ የአሸናፊነት ደብዳቤ ከተሰጠው በኋላ ባሉት 5 ቀናት ውስጥ ይመለስላቸዋል::
8. የጨረታው ሳጥን ግንቦት 14 /2012 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ይዘጋል፤
9. የጨረታው ሳጥን ግንቦት 14 /2012 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲሁም ኢንስቲትዩቱ ኦዲትና የስነ ምግባር ባለሙያ በተገኙበት ይከፈታል፤
10. ከጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት በኋላ የሚቀርቡ የመጫረቻ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም።
11. ኢንስቲትዩቱ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
አድራሻ፡– አርበኞች መንገድ ጳውሎስ ሆስፒታል አጠገብ
ስልክ ቁጥር 0112771054/56/ፋክስ 0112758634
የመ.ሣ.ቁ 1242/ 5456 አዲስ አበባ
የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት