የብሔራዊ ግልጽ ወረታ ጥሪ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር፡– ብግጨ/ኢሕጤኢ/ግኬቲ/
የጎመን ቅጠል ገዥ/068/13 ዓ/ም
የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩቱ በ2013 በጀት ዓመት ለእንስሳት መኖነት የሚውል የጎመን ቅጠል በግልጽ ጨረታ ለመግዛት መስፈርቱን የሚያሟሉና በዘርፉ የተሰማሩ ህጋዊ አቅራቢዎችን በግልጽ ጨረታ ጋብዞ እና አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ፡-
- ተጫራቾች የማይመለስ ብር 50.00 (ሃምሳ ብር) በጥሬ ገንዘብ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከኢንስቲትዩቱ ግዥ ኬዝ ቲም ቢሮ ቁጥር 05 ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ዓርብ ጠዋት ከ2፡30 እስከ 6፡30 ሠዓት ከሰዓት በኋላ 7፡30-11፡00 ሰዓት መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ሀ. በግዥ ኤጀንሲ ዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ፣
- ለ. የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፣የዘመኑን ግብር የከፈሱና አግባብነት ያለው የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው::
- ሐ. ታክስ ክሊራንስ (ከግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት ያድጋፍ ደብዳቤ) የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት (TIN NO-)
- 2. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 2,000.00 (ሁለት ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- 3. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ቴክኒካል ፕሮፖዛል አንድ ኦርጂናል አንድ ኮፒ ፣ፋይናንሽያል ፕሮፖዛል አንድ ኦርጂናል፣ አንድ ኮፒ ሰነዶችን አስፈላጊ መረጃዎችን ሁሉ በማካተት እና በማሸግ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ታኅሣሥ 20 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ከኢንስቲትዩቱ ግዥ ኬዝ ቲም ቢሮ ቁጥር 05 ማስገባት አለባቸው፡፡
- 4. የጨረታው አሸናፊ ሆነው የተመረጡ ድርጅቶች የጨረታው ውጤት በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ10 ቀናት ውስጥ በኢንስቲትዩቱ ግዥ ኬዝ ቲም በመቅረብ ያሸነፉበትን ዋጋ 10% ለመልካም ሥራ አፈፃፀም ዋስትና በማስያዝ ውል መፈረም ኣለባቸው፡፡
- 5 የጨረታው አሸናፊ የሆኑ ድርጅቶች በፈረሙት ውል መሠረት በራሳቸው ትራንስፖርት የተጠቀሰዉን ዕቃ ኢንስቲትዩቱ ዕቃ ግምጃ ቤት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- 6. የጨረታው አሸናፊ ያልሆኑ ድርጅቶች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፒኦ የጨረታ አሸናፊው ተለይቶ የአሸናፊነት ደብዳቤ ከተሰጠው በኋላ ባሉት 5 ቀናት ውስጥ ይመለስላቸዋል፡፡
- 7. የጨረታው ሳጥን ታኅሣሥ 20 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ይዘጋል፡ ፡
- 8. የጨረታው ሳጥን ታኅሣሥ 20 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲሁም የኢንስቲትዩቱ ኦዲትና የስነ ምግባር ባለሙያ በተገኘበት ይከፈታል፡፡
- 9 ከጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት በኋላ የሚቀርቡ የመጫረቻ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡
- 10. ኢንስቲትዩቱ በሙሉም ሆነ በከፊል ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡– አርበኞች መንገድ ጳውሎስ ሆስፒታል አጠገብ
ስልክ ቁጥር፡-0112771054/56
ፋክስ፡0112758634
የመ.ሣ.ቁ፡-1242
አዲስ አበባ
ኢትዮጵያ
የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና
ኢንስቲትዩት