በድጋሚ የወጣ የብሔራዊ ግልፅ ጨረታ
ጥሪ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር፡– ብግጨ/ኢሕጤኢ/ ግኬቲ/ሪኤጀንት/038/2012 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩቱ በ2012 በጀት ዓመት
- የተለያዩ ዓይነት የኬሚካል ሪኤጀንቶችንና ኢኪዩፕመንቶችን
በግልጽ ጨረታ ለመግዛት መስፈርቱን የሚያሟሉና በዘርፉ የተሰማሩ ህጋዊ እቅራቢዎችን በግልፅ ጨረታ ጋብዞ እና አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ፡፡
ስለሆነም በዚህ ጨረታ መሣተፍ የሚፈልጉ፡-
1.ተጫራቾች የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በጥሬ ገንዘብ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከኢንስቲትዩቱ ግዥ ኬዝ ቲም ቢሮ ቁጥር 05 ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት ከ2፡30 እስከ 6፡30 ሠዓት ከሰዓት በኋላ 7፡30-11፡00 ሰዓት መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ሀ. በግዥ ኤጀንሲ ዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ፤
- ለ. የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፣የዘመኑን ግብር የከፈሉና አግባብነት ያለው የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ሐ. ታክስ ክሊራንስ (ከግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት የድጋፍ ደብዳቤ) የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት (TIN NO-)
- መ. ከኤፍኤማካ (FMHACA) የሚሰጥ ሰርተፍኬት
2. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በባንክ ዋስትና ለ60 ቀናት ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
3. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ቴክኒካል ፕሮፖዛል አንድ ኦርጅናል አንድ ኮፒ ፋይናንሺያል ፕሮፖዛል አንድ ኦርጅናል አንድ ኮፒ ሰነዶችን አስፈላጊ መረጃዎችን ሁሉ በማካተት እና በማሸግ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ግንቦት 28/2012 ዓ.ም ድረስ ከኢንስቲትዩቱ ግዥ ኬዝ ቲም ቢሮ ቁጥር 05 ማስገባት አለባቸው፡፡
4. የጨረታው አሸናፊ ሆነው የተመረጡ ድርጅቶች የጨረታው ውጤት በደብዳቤ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ ስራ ቀናት ውስጥ በኢንስቲትዩቱ ግዥ ኬዝ ቲም በመቅረብ ያሸነፉበትን ዋጋ 10% ለመልካም ሥራ አፈፃፀም ዋስትና በማስያዝ ውል መፈረም አለባቸው፡፡
5. የጨረታው አሸናፊ የሆኑ ድርጅቶች በፈረሙት ውል መሠረት በራሳቸው ትራንስፖርት አሸናፊ የሆኑባቸውን የሪኤጀንት ዕቃዎች ኢንስቲትዩቱ ዕቃ ግምጃ ቤት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡
6. የጨረታው አሸናፊ ያልሆኑ ድርጅቶች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፒኦ የጨረታ አሸናፊው ተለይቶ የአሸናፊነት ደብዳቤ ከተሰጠው በኋላ ባሉት 5 ቀናት ውስጥ ይመለስላቸዋል፡፡
7. የጨረታው ሳጥን ግንቦት 28/2012 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ይዘጋል፡፡
8. የጨረታው ሳጥን ግንቦት 28/2012 ዓም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲሁም የኢንስቲትዩቱ ኦዲትና የስነ ምግባር ባለሙያ በተገኙበት ያከፈታል፡፡
9. ከጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት በኋላ የሚቀርቡ የመጫረቻ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡
10. ኢንስቲትዩቱ በሙሉም ሆነ በከፊል ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩቱ
አድራሻ፡– አርበኞች መንገድ
ጳውሎስ ሆስፒታል አጠገብ
ስልክ ቁጥር፡– 0112771054/56
ፋክስ፡-0112758634
የመ.ሣ.ቁ 1242
አዲስ አበባ
የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት