የጨረታ ጥሪ
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስተዳድር የኢሉአባቦር ዞን የመቱ ከተማ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት በስሩ ላሉት መ/ቤቶች ለ2013 ዓም የበጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል
- የተለያዩ የጽህፈት መሣሪያዎች፣
- የጽዳት ዕቃዎች፤
- ፈርኒቸሮች፤
- ኤሌክትሮኒክሶች፤
- ሞተር ሳይክሎች፣
- ጎማዎች እና
- የተለያዩ የመኪና መለዋወጫዎቸ አና
- የሠራተኞች የደንብ ልብስ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ድርጅቶች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
ተቁ |
ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይበት ቀን |
ጨረታው የሚዘጋበት ቀንና ሰዓት |
የዕቃዎቹ ዓይነት
|
የጨረታው ዓይነት |
የጨረታው መክፍቻ ቀን |
1 |
22/12/2012 እስከ 07/01/2013 |
በ8/01/2013 4፡30 ሰዓት |
የጽህፈት መሣሪያዎች፤ |
1 |
በ11/01/2013 በ3፡30 ሰዓት |
2 |
,, |
,, |
የጽዳት ዕቃዎች፤ |
2 |
,, |
3 |
,, |
,, |
ፈርኒቸሮች |
3 |
,, |
4 |
,, |
,, |
ኤሌክትሮኒክሶች |
4 |
,, |
5 |
,, |
,, |
የደንብ ልብስ |
5 |
,, |
6 |
,, |
,, |
ሞተር ሳይክሎች እና ሳይክሎች |
9 |
,, |
7 |
,, |
,, |
የተለያዩ ጎማዎች |
7 |
,, |
8 |
,, |
,, |
የተለያዩ የመኪና መለዋወጫዎቸ |
8 |
,, |
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያለው ፤ የዘመኑን ግብር የከፈለና ማስረጃ አያይዞ ማቅረብ የሚችል እና የቫት (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ፡፡
- በንግድ ሚኒስቴር በአቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገበ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
- ለጨረታ ማስከበሪያ አስር ሺህ(10,000) ብር በሲፒኦ(cpo) ማስያዝ የሚችልና ጨረታውን ካሸነፈ በኋላ ለውል ማስከበሪያ ያሸነፈበትን እቃ ጠቅላላ ዋጋ 10% በባንክ በተመሰከረ ሲፒኦ (cpo) ማስያዝ የሚችል፡፡
- ተጫራቹ ጨረታውን ካሸነፈቀርቦ ውል ለመፈረም ፈቃደኛ የሆነና ዕቃዎቹን በራሱ ሙሉ ወጪ በታዘዘ ጊዜ ውስጥ እስከ ጽ/ቤቱ ለማቅረብና ቆጥሮ ለማስረከብ ፈቃደኛ የሆነ ፡፡
- ተጫራቹ የእቃው ሞዴል ባልተገለጸበት ቦታ በጨረታው ዝርዝር ላይ መግለፅ አለበት፡፡
- ተጫራቹ የተፈለገውን እቃ ጥራትና ብዛት አሟልተው የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡
- ተጫራቹ ለሚያቀርባቸው የደንብ ልብሶች ለመ/ቤቱ አስፈላጊ ለሆኑ እቃዎች ሳምፕል (ናሙና) ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጠናቆ በዚሁ ቀን በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልፅ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች እያንዳንዱን የጨረታውን ሰነድ በማይመለስ አንድ መቶ (100) ብር በመቱ ከተማ ገቢዎች ጽ/ቤት በመግዛት ከኢሉአባቦር ዞን የመቱ ከተማ ገ/ኢ/ት ጽ/ቤት የሚጫረቱበትን መወዳደሪያ የአንዱን ዋጋ በመሙላት ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
- በሌላ ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ክልክል ነው፡፡
- የሚወዳደሩበት ሰነድ ስርዝ ድልዝ የሌለው እና የሚነበብ መሆን አለበት፡፡
- ተወዳዳሪዎች ዋጋን የሚገልጽ ሰነድ ለየብቻ እና ፍቃድንና የተለያዩ ተፈላጊ ሰነዶችን የሚገልፅ
- ኦርጅናል እና ኮፒ ለየብቻ በሰም በታሸገ በሁለት ፖስታ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ፡– ስልክ ቁጥር፡– 047 441 1733/0925947938 /0917115530
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስተዳድር
የኢሉአባቦር ዞን የመቱ ከተማ ገ/ኢ/ት ጽ/ቤት