ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የአ/ጊስ ከተማ አስተዳደር ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ለ2013 በጀት አመት ለመደበኛ በጀት አገልግሎት የሚውል የተለያዩ ቋሚና አላቂ ዕቃዎችን ማለትም
- ሎት 1. የደንብ ልብስ፣
- ሎት 2. የህትመት ውጤቶች ፣
- ሎት 3. የጽህፈት መሣሪያዎች ወይም አላቂ የቢሮ ዕቃዎች ፣
- ሎት 4. የጽዳት ዕቃዎች፣
- ሎት 5. የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች እና ጀኔሬተርን ጨምሮ ፣
- ሎት 6. ተገጣጣሚ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ በየሎታቸው መስፈርቱን ከሚያሟሉ ነጋዴዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ የሚከተሉትን መሰፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በየዘርፉ የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው
- የዘመኑ ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይት የተመዘገቡ መሆናቸውና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከቁ 1-2 የተጠቀሱትን የሚመለከታቸው ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የዕቃው አይነት ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፍኬሽን/ እና ናሙና የሚያስፈልጋቸው ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ለእያንዳንዱ ሎት 20፡00 በመክፈል ከአ/ጊስ ከተማ አስተዳደር ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ማግኘት ይቻላሉ፡፡ የሚገዙ የዕቃዎችን ዓይነት እና ዝርዝር ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ስርዝ ድልዝ ወይም በፉልዱ የተስተካከለ ከሆነ ሰነዱ ተቀባይነት የለውም ወይም መፈረም አለበት፡፡
- መ/ቤቱ አሸናፊውን በነጠላ ወይም በሎት የመለየት መብት አለው፡፡
- አሸናፊው ዕቃዎችን አ/ጊስ ከተማ አስተዳደር ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ድረስ ከጎንደር 40 ኪ.ሜትር ይዘው እንዲመጡ ይደረጋል፡፡ ከታዘዘው ዕቃ ወይም እስፔስፍኬሽን ውጭ ቢያቀርቡ በራሱ ወጭ ዕቃውን ወስዶ ቀይሮ ማምጣት አለበት፡፡
- የባለሙያ ፍተሻ የሚያስፈልጋቸውን በባለሙያ ተረጋግጠው ወደ ንብረት ክፍል የሚገቡ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በአ/ጊስ ከተማ አስተዳደር ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት በገ/ያዥ በመ/ሂ1 ገቢ በማድረግ ገቢ ያረጉትን ኮፒ ከፖስታው ጋር አስገብቶ ማቅረብ አለበት ደረቅ ቼክ እና ሌሎች ተቀባይነት የላቸውም፡፡
- በጨረታ 1ኛ የወጣውን ውል እስከ ሚወስዱ ድረስ 2ኛ የወጣው የጨረታ ማስከበሪያ አይመለስለትም፡፡
- አሸናፊው አሸናፊነቱን ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ አምስት ቀናት ውስጥ ውል መውሰድ አለባት፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ማለትም ኦርጅናል እና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በአ/ጊስ ከተማ አስተዳደር ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት 7/3/2013 ዓ.ም እስከ 21/03/2013 ዓ.ም ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ጨረታውን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቀን 22/03/2013 ዓ.ም በተዘጋጀው ሳጥን ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ይከፈታል፡፡ ተጫራች ባይገኙም ጨረታው ከመክፈት አያግደም ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ብሔራዊ በዓል ከሆነ የሚቀጥለው ቀን ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በአ/ጊስ ከተማ አስተዳደር ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 92 16 18 93 ወይም 058 118 08 46 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአ/ጊስ ከተማ አስተዳደር ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት