የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01
የአ/ክ/ከ/ወ 10 ፋ/ጽ/ቤት ለ2013 ዓ.ም
- የቢሮ የጽህፈት መሳሪያዎች፤
- የደንብ ልብስ፤
- የፅዳት እቃዎች እና ቋሚ የጽሕፈት መሳሪያዎች እንዲሁም ሌሎች የመገልገያ መሳሪያዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ስለሚፈልግ በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላችሁ የዘመኑን ግብር የከፈላችሁ ና ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ህጋዊ ተጫራቾች የሆኑ ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰአት ከወረዳው ፋ/ጽ/ቤት አዲሱ ህንጻ ቢሮ ቁጥር 06 በመቅረብ በማይመለስ 100 /አንድ መቶ ብር / የጨረታ ሰነዱን መግዛት የምትችሉ መሆኑን የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5,000 /አምስት ሺህ ብር/ በCPO ከጨረታ ሰነዱ ኦርጅናልና ኮፒውን ለየብቻው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የታሸገ ለድርጅቱ ማቅረብ አለባችሁ።
ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ሰነዱን መግዛት የምትችሉ ሲሆን በአስራ አንደኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል::
ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ::
ለበለጠ ማብራሪያ፤
በስልክ ቁጥር፡– 0111-56-94-40 ይደውሉ
አድራሻ፡ፒያሳ በሲኒማ አምፓየር ወደ ውስጥ ገባ ብሎ
በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የወረዳ 10 ፋይናንስ ጽ/ቤት