የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር 01/2013
የአጋዝያንቁ3 2ኛ ደ/ት/ቤት በ2013 በጀት ዓመት የሚከተሉትን እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- አላቂ የትምህርት እቃዎችን፣
- አላቂ የጽዳት እቃዎችን፣
- የደንብ ልብስ፣
- የስፖርት ትጥቅ እቃዎችን እና ልዩ ልዩ መሳሪያ እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሰረት በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ሁኔታዎች በቅድሚያ ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡
- በተሰማሩበት የስራ መስክ የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውና ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- በመንግስት ግዥ ኤጀንሲ የንግድ ምዝገባ ማስረጃ ያላቸውና ባቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ፡፡
- የቫት ተመዝጋቢ ለመሆናቸው የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- በመንግስት ጨረታ ላይ የመሳተፍ ጊዜ ያላለፈበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚያገለግሉ የሚጫረቱበትን የእቃ ዋጋውን ብር 5000.00/አምስት ሺ ብር/ በጽሕፈት ቤቱ ስም የተዘጋጀ /ሲፒኦ/ወይም በጽሕፈት ቤቱ ፋይናንስ በካሽ በማስያዝ ማረጋገጫውን ከመወዳደሪያው ሰነዶቻቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የምታስቡአቸው ሰነዶች ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ ሊኖረው አይገባም፡፡ ስርዝ ድልዝ ያለው ሆድ ውድቅ ነው የሚሆነው፡፡
- ከላይ የተጠቀሱት እቃዎች ዝርዝር የሚያሳውቅና የግዥ መመሪያ የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 50.00/ሃምሳ ብር/በመከፈል ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት /ግ/ኣ/ጽ/ቤት ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ዝርዝር የተጻፈ ሰነድ በኢጋዝያን ቁ3 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ፋይናንስ ግዥና ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 1 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጋዜጣው በወጣበት በ11ኛው በአስራአንደኛው የስራቀን ጨረታው በዕለቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአጋዝያን ቁ3 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ፋይናንስ ግዥና ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 1 ይከፈታል፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ የግዥ ዘዴ ካገኘ በሙሉም ሆነ በከፊል መሠረዝ ይችላል፡፡
- ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0111-11-01-23 /0111-11-42-10/0931-58-1181 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በአራዳ ክፍለ ከተማ ት/ጽ/ቤት የአጋዝያን ቁ.3
2ኛ ደረጃ ት/ቤት የፋይናንስ ግዥና ንብረት
አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት