የጨረታ ማስታወቂያ
የሲዳማ ክልላዊ መንግስት በሀዋሳ ከተማ የአዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
- የፅዳት ዕቃዎች ግዥ
- የስቴሽነሪ ዕቃዎች ግዥ
- የህትመት ግዥ
- የደንብ ልብስ ግዥ
- የሜድካል ዕቃዎች ጥገና
- የመድኃኒት ግዥ እና የሬጀንት ግዥ
- የህክምና መገልገያ መሳርያዎች ግዥ
ተጫራቾች:
- ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያለው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
- እንደ አስፈላግነቱ የቫት ተመዝጋቢ የሆነች፡፡
- በመስኩ ሥራ የተሰማሩ፡፡
ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ለCPO 5,000 ( አምስት ሺህ ብር) ማስያዝ አለባቸው፡፡ የጨረታ ሰነዱ አዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል ግዥ ክፍል በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
የጨረታ ሰነድ በሰም ለየብቻው በታሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦርጅናል ሁለት ኮፒ ለየብቻ ፋይናንሻል እና ቴክንካል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ጨረታው በ16ኛው ቀን ጠዋት ከ2፡30 እስከ 6፡00 ሰዓት አዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል ግዥ ክፍል ለጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ እንዲያስገቡ ሆኖ ጨረታው በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን ቅዳሜ ወይም እሁድ እንዲሁም የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
ማሳሰቢያ:
ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙ ጨረታው ተከፍቶ ውሳኔ ይሰጣል፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው፡፡
ለበለጠ መረጃ የስልክ ቁጥር 046212 2371
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት
የሀዋሳ ከተማ የአዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል