የግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 01/2013
የአዳማ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት የጋራዥ አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ከዚህ በታች በተዘረዘረው መሠረት፡
- ተጫራቾች ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር TIN/ የምስክር ወረቀት ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት ያላቸው እንዲሁም የዘመኑን ግብር የከፈሉና ግዴታቸውን የተወጡ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ይህ ጨረታ በማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት 15ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 100 አንድ መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ከልቻ ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር ቅጥር ግቢ በሚገኘው አዳማ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ ቤት ቢሮ ቁጥር 31 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጐ በዛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በግዥና ፋይናንስ . ቡድን ቢሮ ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጐ ይከፈታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ለመጫረት ያቀረበውን አጠቃላይ 2% በባንከ የተመሰከረለት ቼክ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ በአዳማ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ስም አሰርቶ ማቅረብ አለበት፡፡ ቅ/ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
መረጃ የግዥና ፋይናንስ አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 31
ስልክ ቁጥር 022-2-11-58-90
የአዳማ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት