በድጋሚ የወጣ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 03/2013
የአዳማ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት የጋራዥ አገልግሎት በድጋሚ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ከዚህ በታች በተዘረዘረው መሠረት፡-
- ተጫራቾች ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር TIN/ የምስክር ወረቀት ያላቸው ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት ያላቸው እንዲሁም የዘመኑን ግብር የከፈሉና ግዴታቸውን የተወጡ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ይህ ጨረታ በማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት 15 ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ከልቻ ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር ቅጥር ግቢ በሚገኘው አዳማ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 31 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጐ በዛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በግዥና ፋይናንስ ቡድን ቢሮ ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጐ ይከፈታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ለመጫረት ያቀረበውን አጠቃላይ 2% በባንክ የተመሰከረለት ቼክ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ በአዳማ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ስም ኣሰርቶ ማቅረብ አለበት፡፡
ቅ/ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ፡-
የግዥና ፋይናንስ አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 31 አዳማ
ስልክ ቁጥር 022-2-11-58-90
የአዳማ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት