የጨረታ ማስታወቂያ
የአዳማ ወረዳ ገ/ኢ/ልማት/ጽ/ቤት ለ2013 የበጀት ዓመት ለወረዳችን የሚያስፈልጉትን
- የደንብ ልብስ፣
- የጽህፈት መሳሪያ፣
- የጽዳት እቃዎችን፣
- የኤሌክትሮኒክስ፣
- ፈርኒቸሮች ፤
- የትምህርት እቃዎችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
ከላይ የተጠቀሱትን እቃዎችን ማቅረብ ለምትፈልጉ ሁሉ
- የታደሰ የዘመኑን የንግድ ፍቃድ የ2012 ዓ.ም ግብር የተከፈለበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
- ተጫራቾች የቫት(ቲኦቲ) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
- በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መመዝገቡን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ የተረጋገጠ CPO (certify payment vouture) ማስያዝ አለባቸው።
- አሸናፊው ድርጅት በራሱ ወጪ ዕቃውን ለአዳማ ወረዳ ገኢ/ልማት/ጽ/ቤት ድረስ በማቅረብ አስፈላጊ ወጪውን የትራንስፖርት የማውረጃ ይሸፍናል።
- አሸናፊው ድርጅት ጥራቱን ያልጠበቀ እቃ ካቀረበ በራሱ ወጪ የመለወጥ ግዴታ አለበት።
- መ/ቤቱ ካቀረበው ሰነድ ውጪ በሌላ ሰነድ በአማራጭነት ማቅረብ አይችልም።
- አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ አለበት።
- ተጫራቾች የእቃውን ናሙና ሰነዱን በሚያስገቡበት ጊዜ ማቅረብ አለባቸው።
- -ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15(አስራ አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 150(አንድ መቶ ሀምሳ) በመክፈል ከአዳማ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 1 ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- ጨረታው የሚዘጋው በ21/12/2012 በ6፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ እለት በ8፡00 ሰዓት የሚከፈት መሆኑን እናሳውቃለን።
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረገዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ መረጃ የአዳማ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት። የስልክ ቁጥር 0221127908/ 0221112169 በመደወል መጠየቅ ይቻላል።
አድራሻ መብራት ኃይል ንግድ ምክር ቤት አዳራሽ ፈት ለፊት
በምስራቅ ሸዋ ዞን አስተዳደር የአዳማ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት