ለሁለተኛ ግዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የአዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ለ2013 የበጀት ዓመት ከዚህ በታች የተገለጸውን የኤሌክትሮኒክስ ዕቃ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- LED Outdoor digital Display signage በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩት መስፈርቶች የምታሟሉ ነጋዴዎች መወዳደር ትችላላችሁ –
- 2012/2013 ዓ.ም የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ በዘርፉ ያላቸው እንዲሁም የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈለላችሁ፡
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) እና ተርን ኦቨር(TOT) ታክስ ተመዝጋቢ የሆናችሁ ያሸነፉበትን ዕቃ ግዢ መ/ቤት ድረስ በራሳቸው ወጪ ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የጨረታ ሰነድ ኮፒና ኦርጂናሉን ለየብቻ በተለያየ ፖስታ ማሸግ አለባቸው
- ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከኮሌጁ ግዥና ፋይናንስ ከፍል ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ 50 /ሃምሳ ብር እየከፈሉ እስከ 13/4/2013 ስድስት ሰዓት ድረስ የጨረታውን ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡
- ጨረታው የሚከፈተው በ13/4/2013 ከቀኑ 8፡30 በስምንት ሰዓት ተኩል ተጫራቶች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል የዋጋው ዝርዝር በመ/ቤቱ ሰነድ ላይ ብቻ መሞላት አለበት
- ለጨረታ ማስከበሪያ ፦ 3000 (ሦስት ሺ) ብር በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ /በካሽ ብቻ ማስያዝ የሚችል መሆን አለበት፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡– 0911366892 ደውለው መረዳት ይችላሉ
የአዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ