የጨረታ ማስታወቂያ
የአዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ለ2013 የበጀት ዓመት ፡
- የተለያዩ የጽዳት ዕቃዎችና
- ስቴሽነሪ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት/ማሰራት ይፈልጋል።
ስስዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ነጋዴዎች መወዳደር ትችላላችሁ።
- 2012/2013 ዓ.ም የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ በዘርፉ ያላቸው እንዲሁም የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ።
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) እና ተርን ኦቨር (TOT) ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆኑ መረጃ ማቅረብ የሚችል።
- ያሸነፉበትን ዕቃ ግዢ መ/ቤት ድረስ በራሳቸው ወጪ ማቅረብ የሚችሉ። ተጫራቾች ለሚጫረቱት ለእያንዳንዱ ሰነድ ኮፒና ኦርጅናሉን ለየብቻ በተለያየ ፖስታ ማሸግ አለባቸው።
- ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከኮሌጁ ግዥና ፋይናንስ ክፍል ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ 100 ብር /መቶ ብር/ እየከፈሉ እስከ 9/12/2012 ስድስት ሰዓት ድረስ የጨረታውን ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው በ9/12/2010 ከቀኑ 8፡30 ስምንት ሰዓት ተኩል ተጫራቾች/ ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
ጨረታ ማስከበሪያ ብር ከታች የተገስጸውን በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ / በካሽ ማስያዝ የሚችል ይሆናል።
- የተለያዩ የጽዳት ዕቃዎች ብር 6,000 (ስድስት ሺህ ብር)
- ለእስቴሽነሪ ብር 5,000 (አምስት ሺህ ብር)
መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
በተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 022-8127098 ደውለው መረዳት ይችላሉ።
የአዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ