የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 11/2012
የአዲስ ዙ ፓርክ ማዕከል ላሉ ለተለያዩ እንስሳቶች (የአንበሳን ጨምሮ) ቀለብ የሚሆን የበሬ ስጋ ለአንድ አመት ውል በማሰር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ::
በመሆኑም የተጠቀሱትን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች ተጋብዘዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ፣የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና ስለግብር አከፋፈል የሚሰጥ ማስረጃ(clearance) ማቅረብ አለበት፡፡
- ተጫራቾች 5000.00 (አምስት ሺ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲፒኦ ወይም ባንክ ጋራንቲ በአዲስ ዙ ፓርክ ማዕከል ስም ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 100 /አንድ መቶ ብር/ ቦሌ ማተሚያ ፊት ለፊት ገባ ብሎ የድሮው ፒኮክ መናፈሻ ጊቢ ውስጥ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው የስራ ቀን 11.30 ሰዓት በመቅረብ መግዛት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ፋይናንሻል እና ቴክኒካል ዶክመንት ኦርጅናልና እና ኮፒ በአንድ ላይ ፖስታ ውስጥ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሳጥኑ እስከሚታሸግበት 11ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ድረስ ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ሳጥኑ ታሽጎ በዚያው ቀን ጠዋት 4፡30 ቦሌ ማተሚያ ፊት ለፊት ገባ ብሎ የድሮው ፒኮክ መናፈሻ ጊቢ በግዥ የስራ ሂደት ቢሮ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- የጨረታ መክፈቻው ቀን ቅዳሜና እሁድ ላይ የሚውል ከሆነ በቀጣዩ ሰኞ በተጠቀሰው ሰዓት ተዘግቶ የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ዘግይቶ የደረሰ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ማዕከሉ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ፡– ስልክ ቁጥር 0115572917|0115572949 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት
የአዲስ ዙ ፓርክ ማዕከል