የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር AKKKPD,/NCB003/2012 ዓ.ም
የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ በ2012 በጀት ዓመት በመምሪያው ስር ለሚገኙትየሕግ እስረኞች ቀለብ አቅርቦት ለመግዛት እና ያገለገሉ ንብረቶችን ለመሸጥ የወጣ ጨረታዎችን በሀገር ውስጥ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛትና መሸጥ የሚፈልግ ሲሆን፡-
ሎት |
የጨረታው አይነት |
የናሙና መለያ |
የጨረታ ማስከበሪያ የገንዘብ መጠን |
|
01 |
የሕግ እስረኞች ቀለብ አቅርቦት ግዢ |
ናሙና የሚቀርብባቸው |
3,600 00 |
00 |
02 |
የተለያዩ ያገለገሉ ንብረቶች (የተሸከርካሪዎች ጎማ፤ ከመነዳሪ ፤ ባትሪና ቸርኬ ) ለመሸጥ፤ |
|
2,600
|
00 |
ስለዚህ፡– ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው፡፡
- በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው መሆን እና በዘርፉ የተሰማሩ ለመሆናቸው በጀርባው ይመልከቱ የሚል ፅሁፍ በግልፅ ማቅረብ አለባቸው::
- የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ፡፡
- ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው::
- የታደሰ የዘመኑን ንግድ ፍቃድ እና የታደሠ የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው::
- የመንግስት መ/ቤቶች ለሚያወጡት ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የአቅራቢዎች የምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ አለባቸው::
- በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ክሊራንስ ማቅረብ አለበት፡፡
- አማራጭ ዋጋ እና አማራጭ ዕቃ በዚህ ጨረታ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ የጨረታ ውጤቱ እንደታወቀ ተመላሽ የሚሆን በሎቱ ፊት ለፊት የተቀመጠውን የገንዘብ መጠን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ተብሎ በተዘጋጀው ከባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- በጨረታ ውጤቱ አሸናፊ መሆኑ ከታወቀ የገንዘብ መጠን 10% የውል ማስከበሪያ ዋስትና ለአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ተብሎ በተዘጋጀው ከባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ቴክኒካል ሰነዶችንና የዋጋ ማቅረቢያዎችን ፋይናሻል/ ሰነዶች በተለያየ ፖስታ ታሽጎ ለየብቻ መቅረብ አለባቸው።
- ማንኛውንም ተጫራቾች የሚያስገባው ሰነድ ፋይናሻል የጨረታ ሰነድ አንድ ኦሪጅናልና አንድ ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማሸግ በፖስታው ላይ የጨረታ ሰነዱን ቁጥር የሚጫረትበትን ዕቃ አይነት በትክክል መፃፍ እንዲሁም በፖስታውና በገዙት ሙሉ የጨረታ ሰነድ ላይ ፈርመውና ማህተም በመምታት ማስገባት ያለበት ሲሆን፣ ስርዝ ድልዝ በፍሉድ የጠፋ ሰነድ ዋጋ ያልተሞላበት ዝርዝር ተቀባይነት የሌለው መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚያሲዙት ሲፒኢ ከቴክኒክ ሰነዶችጋር በአንድ ላይ ታሽገው መቅረብ አለባቸው::
- በጨረታ አሸናፊ የሆኑ ድርጅቶች ዕቃውን ወይም አገልግሎቱን በራሳቸው ትራንስፖርት አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በሚገኘው የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ግምጃ ቤት ወይም በከፍል 6 በፍላጎት መግለጫው በተጠቀሰው የማስረከቢያ ቦታ ድረስ በማምጣት ማስረከብ አለባቸው፡፡
- በጨረታ ሰነድ በክፍል 6 ውስጥ በሚገኘው የፍላጎት መግለጫ ላይ በሚገለፀው መሰረት ጨረታ ሰነዱ ላይ በቀረበው መሰረት ናሙና ማቅረብ አለበት::
- ተጫራቾች ያቀረቡት ናሙናም ሆነ አሸናፊ መሆናቸው ሲረጋገጥ የሚያቀርቡአቸው ዕቃዎች ፖሊስ መምሪያው ባወጣው ፍላጎት መግለጫ / specification/ መሰረት መሆኑን በመምሪያው የጥራት ኮሚቴ ወይም በኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ኤጀንሲ አማካኝነት የሚረጋገጥ ይሆናል፡፡
- ናሙናው ገቢ መሆን ያለበት ጨረታው ከሚከፈትበት ከአንድ ቀን በፊት መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች ጎጃም በረንዳ አስፋው ወሰን ሆቴል ጎን በሚገኘው መ/ቤት 5ኛ ፎቅ ግዢ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 10 ቀርበው በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ እንዲሁም በማግስቱ በ11ኛው ቀን እስከ ጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ጨረታው ክፍት ሆኖ ስለሚቆይ በመምሪያው ፋይናንስና ግዢ 5ኛ ፎቅ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- በጨረታ ሰነዱ ክፍል 2 ላይ በሚጠቀሰው ቀን በ2012 ዓ.ም ጠዋት በ4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በ4፡30 ሰዓት ሲሆን በመ/ቤቱ 5ኛ ፎቅ ትንሹ አዳራሽ ቢሮ ቁጥር 10 ይከፈታል፡፡
- የጨረታው