የጥበቃ አገልግሎት አቅርቦት ግዢ ጨረታ
የግዥ መለያ ቁጥር ፡-AAU/NCB/SEC/32/12/20
- ሎት- ለዋናው ግቢ እና ጥርስ ህክምና ት/ቤት የጥበቃ አገልግሎት ግዥ
- ሎት-2 ለቢዝነስ እና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ እና ያሬድ ሙዚቃ ት/ቤት የጥበቃ አገልግሎት ግዥ
- የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከላይ የተጠቀሰውን የጥበቃ አገልግሎት አቅርቦት በማዕቀፍ ስምምነት ለመግዛት ይፈልጋል።
- የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጥበቃ አገልግሎት አቅርቦት ለማቅረብ ብቃት ያላቸው ተጫራቶች በታሸገ የጨረታ ሰነድ ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ግዥ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት እንድታቀርቡ ትጋበዛላችሁ።
- ጨረታው የሚከናወነው በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ መንግሥት የመንግሥት የጨረታ ግዥ አዋጅ በተገለጸው የብሄራዊ ግልፅ ጨረታ ሥነ ሥርዓት መሠረት ይፈጸማል።
- የጨረታ ሠነድ ለማስገባት ከዚህ በታች በቁጥር 6 «ለ» በተገለፀው አድራሻ ሰኔ 16 ቀን 2012 ዓ.ም በ4፡00 ሰዓት ወይም በፊት ማስገባት ይችላሉ። ዘግይተው የቀረቡ የጨረታ መልሶች ተቀባይነት የላቸውም። በጨረታው ላይ ለመገኘት በፈለጉ ተጫራቶች ወይም የተጫራቶች ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በቁጥር 6 «ሔ በተጠቀሰው አድራሻ ሰኔ 16 ቀን 2012 ዓ.ም. በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል። የጨረታው ሰነድ የሚላከው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ግዥ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ድረስ በመምጣት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማስገባት ይሆናል።
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ተጫራቶች ብር 30,000.00/ሰላሳ ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ ዋስትና ወይም በሲፒኦ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ሠነድ በተመለከተ፡
- ሀ/ ሰነዶቹ የሚወሰዱት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ግዥ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 313
- ለ/ ጨረታው የሚገባው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 200
- ሐ/ ጨረታው የሚከፈተው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 200
7) የጨረታ ሰነዱን አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ግዥ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ድረስ ዘወትር በስራ ሰአት 2፡30 እስከ 7፡00 ሰዓት ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
8) አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብት አለው::
- ስልክ ቁጥር 0111220001/0111243272
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ግዥ
አስተዳደር ዳይሬክቶሬት