የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር REBID/NCB/GOV/NCS004/2013
የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን አዲስ ላዋቀረው ለሚ ኩራ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከሲ ኤም ሲ አደባባይ እስከ አያት አደባባይ እንዲሁም ሰሚት ኮንዶሚኒየም አካባቢ በዝርዝር በጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለጸው አግባብ የቢሮ ኪራይ አገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አከራዮች በወረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
- ተጫራቾች ዘወትር በሥራ ሰዓት መገናኛ ከሚገኘው ዋና መ/ቤት ምድር ቢሮ ቁጥር 113 በመገኘት ከላይ ለተጠቀሰው ግዥ የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ህጋዊነቱን ለማረጋገጥ የሚከተሉትን ሰነዶች ማቅረብ አለበት አዲስ አከራይ ከሆነ የህንጻ ባለቤትነት ማረጋገጫ ሰነድ ነባር አከራይ ከሆነ የስራ ዘርፍ የሚያሳይ ለዘመኑ ሕጋዊ እና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር ሰብሳቢው ባለስልጣን የተሰጠ ማስረጃ በመወዳደሪያ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማድረግ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ጨረታውን ለመሳተፍ በቅድሚያ ብር 50,000.00/ሃምሳ ሺህ ብር/ የጨረታ ዋስትና የሚሆን ቢያንስ ለ90 ቀናት ጸንቶ የሚቆይ በCPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ይህንኑም እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ከዋናው ሠነድ ጋር በማያያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለበት፡፡
- የተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሠነድ ለ60/ስልሳ/ ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን አለበት፡፡ ከዚህ ያነሰ የጨረታ ዋጋ ፀንቶ መቆያ ጊዜ ያቀረበ ተጫራች ከጨረታው ይሰረዛል፡፡
- የጨረታ ሠነዱን በስሙ አስመዝግቦ ያልገዛ ማንኛውም ተወዳዳሪ በጨረታዉ መሳተፍ አይችልም፡፡
- ጨረታው ጥር 05 ቀን 2013 ዓ.ም ከሰዓት 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኘበት በዕለቱ ከሰዓት 8፡30 ሰዓት 4ኛ ፎቅ በመ/ቤቱ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ከጨረታው መዝጊያ ሰዓትና ቀን ዘግይቶ የሚመጣ ማንኛውም የመወዳደሪያ ሠነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- የሚቀርበው ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስን ያካተተ መሆን አለመሆኑን በግልጽ ተለይቶ መቀመጥ አለበት፡፡ ይህንን ያልገለፀ ተወዳዳሪ ያቀረበው ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታከስን እንዳካተተ ተደርጐ ይቆጠራል።፡
- ገዥው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ የተጠቀሰትን ዕቃዎች በ20% የመጨመር ወይም በ20 % የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የባለስልጣን መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፈል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡ መናኛ በሚገኘው በተለምዶ 24 ቀበሌ የገቢዎች ሚኒስቴር አጠገብ ያለው ሰማያዊ ህንጻ ምድር ቢሮ ቁጥር 113ቁጥር
ስልክ ቁጥር፡-0116-63-0857,ከስ ቀጥር፡-0116 623924
የአዲስ አበባ ውሃና
ፍሳሽ ባለሥልጣን