Construction Machinery / Construction Machinery and Equipment / Machinery and Equipment / Water Engineering Machinery and Equipment / Water Well Drilling

የአዲስ አበባ ወሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን በማዕቀፍ ስምምነት በ2 ዓመት በሚቆይ የወል ጊዜ ማውንት ክሬን ኪራይ (ዕቃዎችን የመጫን፣ የማውረድ፤ ከውሃ ጉድጓድ ማውጣት ሥራ) ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

የጨረታ ማስታወቂያ 

ጨረታ ቁጥር

REBID/NCB/GOV/NCS001/2012 

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን በማዕቀፍ ስምምነት በ2 ዓመት በሚቆይ የወል ጊዜ/ ማውንት ክሬን ኪራይ (ዕቃዎችን የመጫን፣ የማውረድ፤ ከውሃ ጉድጓድ ማውጣት ሥራ) ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ 

ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢዎችን በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡ 

 1. ተጫራቾች ዘወትር በሥራ ሰዓት መገናኛከሚገኘው ዋና መ/ቤት ምድር ቢሮ ቁጥር 13 በመገኘት ከላይ ለተጠቀሰው ግዥ የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ። 
 2. ማንኛውም ተጫራች በመንግሥት የግዥና የንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ በዘርፉ በዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ በድረ-ገፅ የተመዘገበ፤ ለዘመኑ ሕጋዊ እና የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ የምስከር ወረቀት እና የዘመኑን ግብር የከፈሉእና ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር ሰብሳቢው ባለስልጣን የተሰጠ ማስረጃ በመወዳደሪያ ኤንቨሎ ውስጥ በማድረግ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ 
 3. ጨረታውን ለመሳተፍ ብር 15,000.00 /አስራ አምስት ሺ ብር/ የጨረታ ዋስትና የሚሆን ቢያንስ ለ90 ቀናት ጸንቶ የሚቆይ በCPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ይህንኑም እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ከዋናው ሠነድ ጋር በማያያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ወስጥ ማስገባት አለበት፡፡ 
 4. የተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሠነድ ለ60/ስልሣ/ ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን አለበት፡፡ ከዚህ ያነሰ የጨረታ ዋጋ ፀንቶ መቆያ ጊዜ ያቀረበ ተጫራች ከጨረታው ይሰረዛል፡፡ 
 5. የጨረታ ሠነዱን በስሙ አስመዝግቦ ያልገዛ ማንኛውም ተወዳዳሪ በጨረታው መሳተፍ ኣይችልም፡፡ 
 6. ጨረታው ግንቦት 21 ቀን 202 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዕለቱ ከቀኑ በ8፡30 ሰዓት 4ኛ ፎቅ በመ/ቤቱ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ከጨረታው መዝጊያ ሰዓትና ቀን ዘግይቶ የሚመጣ ማንኛውም የመወዳደሪያ ሠነድ ተቀባይነት የለውም፡፡ 
 7. የሚቀርበው ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስን ያካተተ መሆን አለመሆኑን በግልጽ ተለይቶ መቀመጥ አለበት፡፡ ይህንን ያልገለፀ ተወዳዳሪ ያቀረበው ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስን እንዳካተተ ተደርጐ ይቆጠራል፡፡ 
 8. ገዥው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ የተጠቀሱትን ዕቃዎች በ20% የመጨመር ወይም በ20% የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ 
 9. የባለስልጣን መ/ቤቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ 
 • አድራሻ፡- መገናኛ ከሚገኘው በተለምዶ 24 ቀበሌ የገቢዎች ሚኒስቴር አጠገብ ያለው ሰማያዊ ሕንፃ ምድር ቢሮ ቁጥር 113 
 • ስልክ ቁጥር፡- 0116-630857 ፋክስ ቁጥር፡- 0116-623924 

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባስሥልጣን