የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወጣቶችና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ በ2013 በጀት ዓመት ከዚህ በታች በዝርዝር የቀረቡትን የአገልግሎት ግዥዎችን ህጋዊ ከሆኑ አቅራቢዎች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከታች በዝርዝር የተገለጹትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የዘመኑን በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የቫት ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የግብር ከፋይ ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በአቅራቢነት መመዝገባቸውን የሚገልጽ ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከታች በተገለጸው መጠን መሰረት “በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ” ስም በተሰራ ሲፒኦ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
ተ.ቁ |
የዕቃ እና አገልግሎት ግዥ |
የግዥው ምድብ |
የግዥው ሎት ምድብ |
የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ብር |
የመከፈቻ ቀንና ሰዓት |
1 |
የህትመት አገልግሎት አገልግሎት |
አገልግሎት |
ሎት 1 |
50,000 ብር |
በ11ኛው ቀን 4፡30 |
2 |
የሆቴል አገልግሎት አገልግሎት |
አገልግሎት |
ሎት 2 |
30,000 ብር |
በ11ኛው ቀን 4፡30 |
3 |
የጋራዥ አገልግሎት አገልግሎት |
አገልግሎት |
ሎት 3 |
30,000 ብር |
በ11ኛው ቀን 4፡30 |
6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተው በመስሪያ ቤታችን ማለትም /የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወጣቶችና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ/ ሂሳብ ቁጥር 1000003773087 በማስገባት የገባበትን ስሊፕ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዞ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ ለእያንዳንዳቸው በመከፈል ከቢሮአችን ከግዥ እና ንብረት አስተዳደር ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት በአዲሱ ህንጻ 4ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 403 በመቅረብ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን አሟልቶ ኦርጅናል እና ኮፒ ዶክመንቶችን በታሸገ ፖስታ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
9. ጨረታው አየር ላይ በዋለ በ11ኛው የስራ ቀን በ4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በዚያው እለት ለአገልግሎት ግዥ ምድብ፡ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
10. የጨረታ አሸናፊው እንደታወቀ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ ለአሸናፊዎች ከ7 ቀን በኋላ ይመለሳል፡፡
11. የጨረታ አሸናፊው በተጫራቾች መመሪያ በተጠቀሰው መሰረት የጨረታ አሸናፊነቱ በጽሁፍ በተገለጸ ከ7 /ሰባት/ ቀናት በኋላ አስፈላጊውን የውል ማስከበሪያ ገንዘብ በመያዝ ወዲያውኑ ወደ ስራ ክፍሉ መጥቶ ውል መፈረም አለበት። ይህ ባይፈጸም የጨረታ አሸናፊነቱን በመሰረዝ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ብር ለመንግስት ገቢ ይደረጋል፡፡
12. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
ማስታወሻ
- የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ ማስያዝ የተከለከለ ነው፡፡ በሲፒኦ ያቀረበ ተጫራች ከጨረታው ውጪ ይሆናል፡፡
- አንድ ሰነድ የሚያገለግለው ለአንድ የሎት አይነት ብቻ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ፡– በስልክ ቁጥር 0118-120778 አድራሻ፡–ቅድስተ ማርያም መንገድ ብሄራዊ ሙዚየም ጀርባ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና በጎ ፍቃድ
ማስተባበሪያ ቢሮ