የቴሌቪዥንና የሬዲዮ ስፖት ማሰራጫ
የአየር ሰዓት አገልግሱት ግዥ የሀገር ውስጥ
ግልጽ ጨረታ ድጋሚ የወጣ ጨረታ ቁጥር
አአ/ት/ቢ/ብግጨ/02/2013
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ የሚያከናውናቸውን ተግባራት ለማህበረሰቡ ተደራሽ ለማድረግ የቴሌቪዥንና የሬዲዮ ስፖርት ማሰራጫ አየር ሰዓት ግዥ በሀገር ውስጥ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ተጫራቾች፡-
- በዘርፉ በ2013 ዓመት የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያለው የዘመኑ ግብር የከፈለ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ሰርተፊኬት እና የቫት ተመዝጋቢነት የምስክር ወረቀት፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር ስለ መመዝገባቸው የሚያስረዳ ፕሪንት ኮፒ እና እስከ ጨረታው ማስገቢያ የመጨረሻ ቀን ድረስ የግብር ግዴታቸውን ስለመወጣታቸውና በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሳር ቤት አካባቢ አፍሪካ ህብረት ፊት ለፊት በሚገኘው ዮቴክ ህንጻ 6ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 01 ግዥ፣ ንብረትና ጠቅ/አገ/ዳይሬክቶሬት በአካል በመቅረብ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ብር 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ /የባንክ ዋስትና (unconditional bank guarantee) በማስያዝ እስከ ታህሳስ 2 ቀን 2013 ዓም 8፡00 ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው እስከ ታህሳስ 2 ቀን 2013 ዓ.ም 8፡00 ድረስ አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን ጨረታውም በዚሁ ቀን በ8፡00 ተዘግቶ በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫርተው አሸናፊ ከሆኑ ላሸነፉበት አገልግሎት የመልካም ስራ አፈፃፀም ዋስትና ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር) ለምድብ ሁለት ብር 8,000.00 (ስምንት ሺህ ብር) በሲፒኦ (unconditional bank guarantee) ማስያዝ ግዴታ አለባቸው፡፡
- ሌሎች በዚህ ሰነድ ላይ ያልተጠቀሱ የግዥ መመሪያዎች አዲስ አበባ ከተማ መስተዳደርና በፌዴራል ግዥ አዋጅና መመሪያ መሰረት ተፈጻሚ ይሆናል፡፡
- ጨረታው ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከተከፈተ ከ 120 ቀናት ማነስ የለበትም፡፡
ማሳሰቢያ፡– ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ
ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ፡ ሳር ቤት አፍሪካ ህብረት ፊት ስፊት ዮቴክ ህንጻ 6ተኛ
ፎቅ ቢሮ ቁጥር 01 ገዥ፣ ንብረትና መቅ/አገ/ ዳደሪክቶሪት
ስልከ ቁጥር +251-115575952
አዲስ አበባ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር
የትራንስፖርት ቢሮ