የቴሌቪዥንና የሬዲዮ ስፖት ማሰራጫ የአየር ሰዓትና የሕትመት ውጤቶች ግዥ
የሀገር ውስጥ ግልጽ ጨረታ ጨረታ ቁጥር አ/አ/ት/ቢ/ብግጨ/02/2013
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ የሚያከናውናቸውን ተግባራት ማህበረሰቡ ተደራሽ ለማድረግ የቴሌቪዥንና የሬዲዮ ስፖት ማሰራጫ አየር ሰዓት ግዥ በምድብ አንድ እና የተለያዩ ህትመት ውጤቶችን በምድብ ሁለት በሀገር ውስጥ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ተጫራቾች፡
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያለው የዘመኑ ግብር የከፈለ፣የግብር ከፋይነት መለያ ሰርትፍኬት እና የቫት ተመዝጋቢነት የምስክር ወረቀት፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር ስለ መመዝገባቸው የሚያስረዳ ፕሪንት ኮፒ እና እስከ ጨረታው ማስገቢያ የመጨረሻ ቀን ድረስ የግብር ግዴታቸውን ስለመወጣታቸውና በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፣
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሳር ቤት አካባቢ አፍሪካ ህብረት ፊት ለፊት በሚገኘው ዮቴክ ህንጻ 6ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 01ግዥ፣ ንብረትና ጠቅ/አገ/ዳይሬክቶሬት በአካል በመቅረብ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፣
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ለምድብ አንድ 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር) ለምድብ ሁለት 3,000.00 (ሦስት ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ /የባንክ ዋስትና (unconditional bank guarantee) በማስያዝ እስከ ጥቅምት 17 ቀን 2013 ዓ/ም 8፡00 ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው እስከ ጥቅምት 17 ቀን 2013 ዓ/ም 8፡00 ሰዓት ድረስ አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን ጨረታውም በዚሁ ቀን በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፣
- ተጫርተው አሸናፊ ከሆኑ ላሸነፉበት አገልግሎት የመልካም ስራ አፈፃፀም ዋስትና ለምድብ አንድ ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር) ለምድብ ሁለት ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) በሲፒኦ (unconditional Bank guarantee) ማስያዝ ግዴታ አለባቸው፣
- ሌሎች በዚህ ሰነድ ላይ ያልተጠቀሱ የግዥ መመሪያዎች አዲስ አበባ ከተማ መስተዳደርና በፌዴራል ግዥ አዋጅና መመሪያ መሰረት ተፈጻሚ ይሆናል፣
- ጨረታው ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከተከፈተ ከ20 ቀናት ማነስ የለበትም፣
ማሳሰቢያ፡– ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ ሳር ቤት አፍሪካ ህብረት ፊት ለፊት ዮቴክ ህንጻ 6ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 01ግዥ፣ ንብረትና ጠቅ/አገ/ዳይሬክቶሬት
ስልክ ቁጥር 251-11-557-59-52
አዲስ አበባ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ