ግልፅ የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 01/2013
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምግብ፣ የመድኃኒት፣ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን የ2013 ዓም በጀት ዓመት ለሆቴልና መስተንግዶ አገልግሎት በግልፅ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- ሎት1፡– የሆቴል አገልግሎት ( ለአንድ ዓመት ውል ኮንትራት)
- ሎት 2- መስተንግዶ ውሃ እና ቆሎ (ለአንድ ዓመት)
ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መመዘኛዎች ማሟላት የሚችሉ ድርጅቶች መወዳደር ይችላሉ
- ተጫራቾች በተሠማሩበት የሥራ መስክ ማቅረብ የሚችሉ የዘመኑን ግብር የከፈሉበትንና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፣
- አነስተኛና ጥቃቅን ከአደራጃቸው አካል ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው::
- የመንግሥት የግዥ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ የአቅራቢነት ፈቃድ ያላቸው
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ዝርዝር የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 100/ መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስር ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ከባለሥልጣን መ/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 601 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ማስታወቂያ በወጣ በ10ኛው የሥራ ቀን እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ የመጫረቻ ዋጋ 2% ሲፒኦ የመወዳደሪያ ሰነዶቻቸውን ኦርጂናልና አንድ ኮፒ ሞልተው በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- አሸናፊ ተጫራች የውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን 10 ፐርሰንት ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በ11ኛው የስራ ቀን 4፡00 ታሽጐ በዚሁ ዕለት በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ከገዙት ጨረታ ሰነድ ውጭ ተሞልቶ የመጣ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- አቅራቢዎች ቫትን ከጠቅላላ ዋጋ ላይ አካተው ዋጋቸውን ማቅረብ አለባቸው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ ፡– ቦሌ መንገድ ፍላሚንጐ ጐን ቶሚ ታወር 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 601
ስልክ ቁጥር 0118603257
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምግብ ፣የመድኃኒት፣
ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን