የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር አ/ወ/በ/ማ/ቢ/ግ/ቁ//002/2013
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ ለ2013 በጀት ዓመት የተለያዩ የቢሮ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ ግዥ ዘዴ ከዚህ በታች በዝርዝር የቀረቡትን ዕቃዎች መግዛት ይፈልጋል
በመሆኑም በዝርዝር የቀረቡትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡
ተ.ቁ |
የግዥው ዓይነት
|
የተሰጠው ሎት |
የዕቃው አገልግሎቱ ዓይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ ብር መጠን |
ጨረታው የመክፈቻ ቀንና ሰዓት |
1 |
ዕቃ |
ሎት 1 |
የመጽሀፍ ግዥ |
10,000
|
በ11ኛው ቀን በ4፡30 ሠዓት |
2 |
ዕቃ |
ሎት 2 |
የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ግዥ |
30,000
|
በ11ኛው ቀን በ4፡30 ሠዓት |
3 |
ዕቃ |
ሎት 3 |
የሙዚቃ መሳሪያ ዕቃዎች ግዥ |
10,000
|
በ11ኛው ቀን በ4፡30 ሠዓት |
4 |
ዕቃ |
ሎት 4 |
የባህል አልባሳት ግዥ |
30,000
|
በ11ኛው ቀን በ4፡30 ሠዓት |
5 |
ዕቃ |
ሎት 5 |
መጋረጃና የወለል ምንጣፍ ግዥ |
5,000
|
በ11ኛው ቀን በ4፡30 ሠዓት |
- በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው የዘመኑን ግብር የከፈለ፣ የግብር ከፋይ መለያ ሰርተፍኬትና የቫት ተመዝጋቢ ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ናሙና እንዲያቀርብባቸው የሚፈለጉ ዕቃዎችና አገልግሎቶች ናሙና ማቅረብ ግዴታ ያለባቸው ሲሆን ናሙና በተጠየቀበት ናሙና ያላቀረበ ተጫራች ከውድድር ውጭ ይደረጋል፡፡
- ተጫራቾች በመንግስት ግዥ ለመሳተፍ በግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ድረገጽ ላይ የተመዘገቡና ያልታገዱ መሆናቸውን መረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- መደበኛ ጨረታ ሰነዱ የሚገኝበት ቦታ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ አምስት ኪሎ ቅድስት ማርያም ቤ/ክርስቲያን ወደ ውስጥ ገባ ብሎ በቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን ጀርባ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 403 በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሮክቶሬት ነው፡፡
- የጨረታ ሰነዱ የሚሸጠው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ቀኑ 11፡30 ድረስ ሲሆን ሰነዱን ብር 100 ( መቶ ብር) የሚሸጥ ይሆናል፡፡
- የጨረታ የመዝጊያውና የመክፈቻው በ11ኛው ቀን ጨረታው 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት በ4፡30 በቢሮው አዳራሽ 5ኛ ፎቅ ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ሰነዱን ኦርጅናልና ኮፒ ለየብቻው በተለያያ ፖስታ በሰም በታሸገ ፖስታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቢሮው በከፈተው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ ሂሳብ ቁጥር 1000003773087 በማስገባት ያስገቡበትን ስሊፕ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ መቅረብ ይኖርበታል ::
- የጨረታ ማስረከቢያ በሲ.ፒኦ ማስያዝ የተከለከለ ነው ። በሲፒኦ ያቀረበ ተጫራች ከጨረታ ውጪ ይሆናል
- አንድ ሰነድ የሚያገለግለው ለአንድ የሎት አይነት ብቻ ነው ::
- ቢሮው ጨረታውን የተሻለ መንገድ ካገኘ በከፊል ወይም በመሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ ፦ በስልክ ቁጥር 0118-120778
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ