ግልጽ ጨረታ
የጨረታ ቁጥር ከንቲባ ጽ/ቤት
ግ/ጨ/ቁ/03/2013
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት ለ2013 በጀት ዓመት ሊገዛቸው ያቀደውን የተለያየ ዓይነት ዕቃዎች ግልጽ ጨረታ በማውጣት የጨረታ መስፈርቱን ከሚያሟሉ ድርጅቶች የሚፈለጉ አገልግሎቶች መግዛት ይፈልጋል፡፡
በተጨማሪ ተጫራቾች ቴክኒካልና ፋይናንሽያል ዶክመንት በተለያየ ኤንቨሎፕ በማድረግ ማስገባት አለባቸው፡፡
ተ.ቁ |
የጨረታው ዓይነት ዝርዝር |
ለጨረታ ማስከበሪያ |
ምርመራ |
ሎት1 |
የመኪና ጌጣጌጥ |
5,000 |
|
ሎት2 |
የመኪና ጎማ |
10,000 |
|
ሎት3 |
የህንፃ መሣሪያዎች |
5,000 |
|
ሎት4 |
ህትመት |
30,000 |
|
ሎት5 |
የሴቶች የፕሮቶኮል ልብስ እና ጫማ |
10,000 |
|
ሎት6 |
ምንጣፍና መጋረጃ |
10,000 |
|
ሎት7 |
የጽዳት ዕቃዎች |
5,000 |
|
- ተጫራቾች የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ የንግድ ሥራ ምዝገባ ከሀገር ውስጥ ገቢ ባለሥልጣን የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉና የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ለመሆኑ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 100/አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከንቲባ ጽ/ቤት ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተመሰከረለት የክፍያ ትዕዛዝ (cpo) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት ስም በማሠራት ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ የጨረታ ቁጥርና የዕቃውን ዓይነት በግልጽ ኢንቨሎኘ ላይ በመጻፍ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት የግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 17 በሥራ ሰዓት ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 የጨረታው ሳጥን ተዘግቶ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት ግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 17 ይከፈታል፡፡ የጨረታው መዝጊያና መክፈቻው የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ ይከፍታል፡፡
- ቢሮው ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት /ማዘጋጃ ቤት/ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 17
የ.ሳ.ቁ 356/2445
ስልክ ቁጥር፡-0111118777/ አዲስ አበባ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት