የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር አ/አ/ኢ/ኮ 01/2013
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የግዥ ንብረት አስተዳደር እና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ድጋፍ ለሚሰጣቸው ለስራ ክፍሎች አገልግሎት የሚውሉ
- ሎት 1. አላቂ የፅህፈት እቃዎችና ልዩ ልዩ መሳሪያዎች
- ሎት 2. የፅዳት እቃዎች
- ሎት 3. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
- ሎት 4. የፈርኒቸር እቃዎች
- ሎት 5. የተለያዩ ህትመቶች
- ሎት 6. የደንብ ልብስ
ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች እና ግለሰቦች በጨረታ እንዲሳተፉ ይጋብዛል::
- አግባብነት ያለው የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ እንዲሁም በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ወይም በአ/አ/ከ/አ/ፋይናንስ ቢሮ በእቃ አቅራቢነት ዝርዝር ለመመዝገባቸው ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
- ግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸው እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር
- ለሎት1 ብር 5000.00/ አምስት ሺህ ብር
- ለሎት 2 ብር 3000.00 /ሦስት ሺህ ብር/
- ለሎት 3 ብር 5000.00/ አምስት ሺህ ብር/
- ለሎት 4 ብር 5000.00 / አምስት ሺህ ብር/
- ለሎት 5 ብር 2000.00 /ሁለት ሺህ ብር/
- ለሎት 6. 2000.00 ብቻ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር ለእያንዳንዱ ሎት ብር 50.00/ ሃምሳ ብር በመክፈል ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢንቨስትመንት ኮሚሽን በግዥ ንብረት አስተዳደር እና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት በሠንጋ ተራ/ ዮቤክ ኮሜርሽያል ሴንተር 8ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 801A መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10/አስር/ የስራ ቀናት በአየር ላይ ከዋለ በኋላ በ10ኛው በአስረኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰአት ተዘግቶ በማግስቱ ባለው የሥራ ቀን ጠዋቱ 3፡00 ሰዓት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢንቨስትመንት ኮሚሽን በግዥ ንብረት አስተዳደር እና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት 8ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 802 ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዳቸውን በጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለጸው መሰረት ሞልተው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን እቃዎች ለመለየት የሚያስችል ናሙና ወይም ስፔስፊኬሽን ወይም በፎቶ የተደገፈ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዞ መቅረብ ይኖርበታል።
- አንድ ተጫራች ሌላው ከሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም።
- ተጫራቾች የተጠቀሱትን እቃዎች በሙሉ ወይም በከፊል መጫረት ይችላሉ።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በግዥ ንብረት አስተዳደር እና ጠቅላላ
አገልግሎት ዳይሬክቶሬት 8ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 802 በመቅረብ ወይም
በስልክ ቁጥር 011557-78-46 ደውለው ያነጋግሩ ።
አድራሻ ልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ወረዳ 09 ዮቤክ ኮሜርሽያል ሴንተር
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢንቨስትመንት ኮሚሽን