የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 01/2012
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ማህበራዊ ኮሚቴ የሰራተኞች የመዝናኛ ክበብ አገልግሎትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን ለዚሁ ዓላማ የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ በማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመግዛት በጨረታው መወዳደር ይችላል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ሰርተፍኬት ያለው፡፡
- በካፍቴሪያ መስተንግዶ አቅራቢነት ፍቃድ ያለው፡፡
- የመልካም ሥራ አፈፃፀም ቢያንስ ሁለት ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል፡፡
- የመስሪያ ካፒታል ብር 200,000 እና በላይ /ሁለት መቶ ሺ ብር እና በላይ / የባንክ ዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን በባንክ የተመሰከረ በብር 30,000 በአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ማህበራዊ ኮሚቴ ስም ተዘጋጅቶ ከጨረታ ሠነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ1ዐ ተከታታይ የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ከቢሮአችን የፋይናንስ ዳይሬክቶሬት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 103 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሠነዱን አሟልቶ ኦርጅናልና ኮፒ ዶክመንቶችን በታሸገ ፖስታ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ዘወትር ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት አስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ በፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ለዚሁ ጨረታ፤ አገልግሎት በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለበት፡፡
- ጨረታው በአየር ላይ ከዋለ በ11ኛው ቀን በ3፡30 ሠዓት ታሽጎ በዕለቱ ከረፋዱ 4፡00 ሠዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቢሮ ቁጥር 102 ይከፈታል፡፡ ሆኖም ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ እንደታወቀ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ ለተሸናፊዎች ከ7 ቀናት በኋላ ይመለሳል፡፡
- ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
በተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር፡-0111223884
አድራሻ፡-6 ኪሎ ወደ ጃን ሜዳ በሚወስደው መንገድ ኦሮሚያ ፍርድ ቤት ፊት ለፊት
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ