የጨረታ ማስታወቂያ
ቤ/ል/አስ/ቢሮ ግዥ/ንብ/አስ/ጠ/አ/ግ ቁጥር 01/2013
ለቢሮው አገልግሎት የሚውል
- የተሽከርካሪ ጎማ፣
- አላቂ የቢሮ ዕቃ፣
- የፅዳት ዕቃ፣
- ደንብ ልብስ፤
- የቢሮ ምንጣፍ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት መወዳደር የምትፈልጉ አቅራቢ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ በጨረታ አንድትሳተፉ ተጋብዛችኋል፡፡
- አግባብነት ያለው የታደሠ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ እንዲሁም በአገልግሎት አቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ የምሥክር ወረቀት የሚያቀርቡ ማንኛውም ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ለጨረታ ሰነድ ግዥ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር ብቻ) በቢሮው የፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ክፍል ቀርበው በመክፈልመውሰድ የሚችሉ ሲሆን፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የግዥውን 2% (ሁለት ፐርሰንት) ሲ.ፒ.ኦ አሰርተው ማሲያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ዋናው እና ኮፒውን ለየብቻው በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ለዚህ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ገቢ የሚያደርጉት የጨረታው ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ቀናት ሲሆን የቢሮው የሥራ ቀናት ከሰኞ–አርብ ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ 11:00 ሰዓት መሆኑን እየገለጽን የጨረታ ሰነዱን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ 7ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር-703— ማስገባት አለባቸው::
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትየጨረታው ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ በ11ኛው ቀን ከቀኑ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ በ4፡30 ሰዓት በቢሮው የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ የጨረታው መዝጊያ እና መክፈቻ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል፡፡ በተጨማሪም በጨረታ ሰነዱ የመጀመሪያ ገጽ ላይ ሙሉ መረጃውን መመልከት ይችላሉ፡፡
- ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
አድራሻ:- ባምቢስ ባቡር መሻገሪያ ወደ ደምበል በሚወስደው መንገድ በስተቀኝ ገባ ብሎ
ስልክ ቁጥር+251118-72-3977
የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማት አስተዳደር ቢሮ