Freight Transport / Transportation Service / Vehicle

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በ2013 በጀት ዓመት ለመንገድ ግንባታና ጥገና ስራ የሚያገለግሉ ገልባጭ መኪኖች ተከራይቶ ማሰራት ይፈልጋል

የገልባጭ መኪና ኪራይ አገልግሎት 

ግዥ ጥሪ ማስታወቂያ 

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በ2013 በጀት ዓመት ለመንገድ ግንባታና ጥገና ስራ የሚያገለግሉ ገልባጭ መኪኖች በቁርጥ ዋጋ ከዚህ በታች የተቀመጡትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አከራዮች ተከራይቶ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ 

የመኪናው ዓይነት

ብዛት

 

ዝቅተኛ የመሳሪያው ጉልበት/የመጫን አቅም

የስሪት ዘመን ..

 

1 ./ . ነጠላ ዋጋ ነዳጅ +ቫት

ገልባጭ መኪና

100

>12m3

 

>2010

 

o-5 ኪሜ

4.60

5.01ኪሜ -10ኪ.ሜ

4.60

ከ10ኪሜ በላይ

4.60

  1. ተጫራቾች አግባብነት ያለው ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ ሰርተፊኬት እና የግብር ከፋይ ሰርተፊኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ 
  2. የባለቤትነት ማረጋገጫ ሊብሬ ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ 
  3. መመዝገብ የሚችሉት የተሽከርካሪው ባለቤት ወይም በስማቸው ተሽከርካሪውን ማከራየት እንደሚችሉ በሰነዶች ማረጋገጫ ውክልና የሚያቀርቡ ብቻ ናቸው፡፡ 
  4. ተጫራቾች በከፍያ ወቅት የተጨማሪ እሴት ታክስ (15%) ህጋዊ የገንዘብ መቀበያ ደረሰኝ ማቅረብ አለባቸው፡፡ 
  5. ተጫራቶች እንዳመጣጣቸው ቅደም ተከተል ተመዝግበው በቅደም ተከተሉ መሰረት ለስራው ይጠራሉ፡፡ 
  6. ለኪራይ የቀረበው ገልባጭ መኪና የቴከኒክ ይዘት ከላይ በተጠቀሱት መስፈርቶች መሰረት ስለመሆኑ ባለስልጣን መ/ቤቱ የመሳርያ ኣቅርቦት አስተዳደርና ጥገና ዳይሬከቶሬት እያረጋገጠ ስምሪት የሚሰጥ ይሆናል፡፡ 
  7. የኪራይ አገልግሎት የሚያበቃበት ጊዜ መስከረም 30 ቀን 2014 ዓ.ም ይሆናል፡፡ 
  8. አከራዮች ማስታውቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በስራ ቀናት በባለስልጣኑ መ/ቤት ዕቃ ግዥ አቅርቦትና ንብረት አስተዳደር ዳይሬከቶሬት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 1 ለምዝገባ የሚያስፈልጉትን ማስረጃዎች ኦርጅናል እና ፎቶ ኮፒ ይዘው በመቅረብ መመዝገብ ይኖርባቸዋል፡፡ 
  • መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ የኪራይ አገልግሎቱን በመሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ 
  • ስለተጨማሪ ማብራሪያ በስ.ቁ 0113-72-28-25 /o0113-71-41-03 ይደውሉ 

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን