ለ3 ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የገዥው መለያ ቁጥር እስከመባ/ግብዓት/ቡ –1/0023/2013
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን በ2013 በጀት አመት ለመንገድ ግንባታ አገልግሎት የሚውሉ ከታች የተገለፁትን የኮንስትራክሽን መሣሪያዎች በሰዓት የኪራይ አገልግሎት በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ተቁ |
በሰዓት ለኪራይ የተፈለገ የማሽነሪ ዓይነት |
የስሪት ዘመን
|
ብዛት በቁጥር
|
አጠቃላይ ለኪራይ የሚፈለገው ሰዓት |
የጨረታ መለያ ቁጥር |
ጨረታ ፀንቶ የሚቆይበት
|
የጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት |
የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት |
የጨረታ ማስከበሪያ በብር
|
1 |
Motor Grader (›40Hp) |
>2010 GC
|
1 |
እስከ Meskerem 30 ቀን 2014 ዓ.ም. |
አአከመባ/ግብዓት/ቡ-1/002-3/2013
|
150 ቀን |
ጥር 13 ቀን 2013 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡30 |
ጥር 13 ቀን 2013 ዓ.ም. ከጠዋቱ 5፡00 |
ለአንድ ማሽነሪ 10000.00 /አስር ሺ ብር/ |
2 |
Wheel Excavator > Im3 Bucket capacity and 135Hp) |
>2005 GC
|
4 |
||||||
3 |
Wheel Loader >180 HP |
>2010 GC |
2 |
||||||
4 |
Single Drum Roller (>16 ton) |
>2005 GC
|
5 |
||||||
5 |
Double Drum Roller (› 4 ton) |
>2005 GC
|
4 |
||||||
6 |
Double Drum Roller (› 7 ton) |
>2005 GC
|
1 |
||||||
7 |
Double Drum Roller (› 15 ton) |
>2005 GC
|
4 |
||||||
8 |
Penumatic Roller (›12 ton (Unballasted) |
>2003 GC |
2 |
||||||
9 |
Backhoe Loader (›90 Hp) |
>2005 GC |
2 |
||||||
10 |
Water trucks ›13,000 Lit |
>2005 GC |
5 |
||||||
11 |
High bed with trailer > 35 ton |
>2010 GC |
1 |
||||||
12 |
Aerial plat form crane min. boom length 12 meter 3 |
>2006 GC |
3 |
||||||
13 |
Jet truck (j-truck) > 6000Lit |
>2006 GC |
3 |
ስለዚህ፤
- ተጫራቾች አግባብነት ያለው ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ አግባብነት ያለው የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ከአዲስ አበባ ከተማ ኮንስትራክሽን ቢሮ፤ የግብር ከፋይ ሰርተፍኬት እና በጨረታ መወዳደር የሚያስችል የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ታከስ ክሊራንስ ሰርተፊኬት እንዲሁም በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ስለመመዝገባቸው የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ለመመዝገባቸው ማስረጃ ሰነድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ በተጨማሪም ተጫራቾች በሰዓት ለኪራይ አገልግሎት ለሚወዳደሩባቸው የኮንስትራክሽን መሣሪያዎች የባለቤትነት ማረጋገጫ ሊብሬ ወይም በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ ውልና ማስረጃ የተረጋገጠ የባለቤትነት ማረጋገጫ ሊብሬ ውክልና ማቅረብ የሚችሉ ስለመሆኑ በጨረታ ሰነዱ ከፍል 6/ስድስት/ አባሪ ሁለት በቀረበው ቅፅ መሰረት በማረጋገጥ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ መጀመሪያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከባለሥልጣኑ መ/ቤት የፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 135 መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ዋስትናው ከታወቀ ባንክ በባንክ ጋራንቲ ወይም በCertified Payment Order (CPO) ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ በተጫራቾች የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ተጫራቾች ባቀረቡት የማሽነሪ ብዛት መጠን የሚወሰን ሲሆን፣ ባለስልጣን መ/ቤቱ የተፈለገውን የማሽነሪ ብዛት በሙሉ የሚያቀርቡት የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ከላይ በሰንጠረዥ በተገለፀው መሰረት ይሆናል፡፡ ከባንክ የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) ለ180 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን ይኖርበታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የመጫረቻ ሰነዱን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ከላይ በሰንጠረዥ የጨረታ መዝጊያ ተብሎ እስከ ተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ስባለሥልጣኑ መ/ቤት ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 109 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ከላይ በሰንጠረዥ የጨረታ መከፈቻ ተብሎ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በባለሥልጣኑ ዋና መ/ቤት ይከፈታል፡፡
መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
(ሳርቤት ፑሽኪን አደባባይ አጠገብ)
ስልክ ቁጥር 011-3-71-41-03 /011-3-72-28-15
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን