የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 01/2013
የአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የቅ/ጽ/ቤቱ የ2013 በጀት ዓመት :
- ሎት 1. የቅ/ጽ/ቤቱ የ2013 በጀት ዓመት የሰራተኛ ደንብ ልብስ የሚሆን ሸሚዝ፣ ጫማ፣ የአደጋ መከላከያ እና የጤና መጠበቂያ ዕቃዎች፤
- ሎት2 . አላቂ የቢሮ ዕቃዎች ፤
- ሎት 3.የሕትመት ውጤቶች ፤
- ሎት 4. የጽዳት ዕቃዎች ፤
- ሎት 5 ልዩ ልዩ መሳሪያዎች ፤
- ሎት 6. ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች /ማሽነሪዎች፤
- ሎት 7.ቋሚ የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች ፤
- ሎት 8. ልዩ ልዩ የተሽከርካሪ ጎማዎች፤
- ሎት 9. የቢሮ ፓርቲሽን እና የብረት ሜሽ ስራ፤
- ሎት10. የቢሮ የስልክ ጥገና እና መስመር ዝርጋታ ስራዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ሰለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ማንኛውም ህጋዊ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ከገቢዎች ባለሥልጣንና ጉምሩክ ኮሚሽን የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- በገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ትብብር ሚኒስቴር የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/የምዝገባ ማስረጃ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 100/አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ቦሌ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ካርጎ ተርሚናል 1ኛ ፎቅ የጉምሩክ ግዥና ፋይናንስ ቢሮ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም ቢድ ቦንድ (BID BOND) ከጨረታ ሰነዱ ጋር አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የሚወዳደሩባቸው እቃዎች ጥራታቸውን የጠበቁ መሆን ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች ለሚያቀርቡት እቃና አገልግሎት ግዢዎች በሙሉ ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ከአገልግሎት ግዥዎች በስተቀር ናሙና ሊቀርብላቸው የሚችሉትን እቃዎች በተመለከተ ከእየአይነቱ አንድ አንድ ናሙና የድርጅታቸውን ማህተም አድርገው የናሙናዎቹን ዝርዝር በሁለት ኮፒ በማድረግ ጨረታው ከሚከፈትበት ዕለት አስቀድሞ ለቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ንብረት ሠራተኛ አስፈርመው ማስረከብና አንዱን ኮፒ መረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ለሚወዳደሩባቸው ማንኛውም እቃዎች እና አገልግሎቶች የፋይናንሺያል እና ቴክኒካል ዶክመንት ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- በሰነዶቻቸው ላይስማቸውን፣ሙሉ አድራሻቸውንና ፊርማቸውን አሟልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ የሚቀርብ ዋጋ ተቀባይነት የለውም፡፡
- የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዳቸውን ማስገባት የሚችሉ ሲሆን በዚሁ ቀን 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በ4፡15 ሰዓት ተጫራቾች እና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡ እለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ለአሸናፊ ተወዳዳሪዎች በጨረታው ማሸነፋቸው እንደተገለጸላቸው ቅሬታ ያላቸው ተወዳዳሪዎች ቅሬታቸውን በጽሑፍ ለቅ/ጽ/ቤቱ ስራ አስኪያጅ በ5 ቀናት ውስጥ ማቅረብ ይችላሉ፡፡ በውድድሩ የቀረበ ቅሬታ ከሌለ አሸናፊ ድርጅቶች በ15 ቀናት ውስጥ በቅርንጫፉ ጽ/ቤቱ ቀርበው ግዢውን ከሚፈፅመው አካል ጋር ውል ይፈፅማሉ፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ድርጅት የመልካም ስራ አፈጻፀም ዋስትና 10% (አስር ፐርሰንት) CPO በማስያዝ ከመ/ቤቱ ጋር ዉል ይፈራረማል፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ፡– በስልክ ቁጥር 0116651392/0116651393 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
አድራሻ፡– አዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በቦሌ ሚካኤል መንገድ አሚን ጠቅላላ ሆስፒታል ፊት ለፊት ባለው በካርጎ ቅጥር ግቢ ውስጥ የጉምሩክ ግዥና ፋይናንስ አስተዳደር ቡድን ቢሮ
የአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት