በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር አ/አ/ከ/አስ/ቤ/ል/ኮ 04/2013
የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ለህንጻ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ቋሚ እና አላቂ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም
- ቋሚ የቧንቧ መሣሪያዎች ፣
- ቋሚ የእንጨት ስራ መሣሪያዎች ፣
- ቋሚ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣
- ቋሚ የአታክልተኛ እና የጥበቃ ዕቃዎች፤
- አላቂ የእንጨት ስራ ዕቃዎች፤
- አላቂ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች እና አላቂ የቧንቧ ዕቃዎች መግዛት የሚፈልግ ሲሆን
በዘርፉ የተሠማሩ፤ በዘመኑ የታደሠ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ፤ የአቅራቢነት ዝርዝር ወይም በድረ–ገጽ ላይ የተመዘገቡ ለመሆናቸው ማስረጃ ኮፒ አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶች እና ግለሰቦች የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 100.00 (መቶ ብር) በመክፈል ባንቢስ አካባቢ ግሪክ ት/ቤት ፊት ለፊት በሚገኘው አዲስ ሕንጻ ላይ 4ኛ ፎቅ በኮርፖሬሽኑ የትሬዤሪ ክፍያና ሒሳብ ዳይሬክቶሬት ቢሮ በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 10,000.00 (አስር ሺ ብር 00/100) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ወይንም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ከሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ጋር በማያያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
ጨረታው ህዳር 25 ቀን 2013 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡00 ሠዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሠዓት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ሕንጻ 6ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የኮርፖሬሽኑ የግዥ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ኮርፖሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡– በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 1 ባንቢስ አካባቢ ግሪክ ት/ቤት ፊት ለፊት የሚገኘው አዲስ ሕንፃ
ስልክ ቁጥር 0118-78-79-45
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ
የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን