ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 2/2012
የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፤
- የተለያዩ የፅህፈት መሣሪያዎች ፣ ኮምፒውተሮች ፣ ላፕቶፖች ፣ የኮምፒውተር መለዋወጫዎች፣
- የፅዳት ዕቃዎች ፣ የምርት ማሽጊያ ማዳበሪያ ፣ ፕላስቲክ ከረጢት የድርጅቱ አርማ ያለበት እና የምርት መገልገያዎች(ጋሪ፣አካፋ፣
- የደንብ ልብስ ስፌት ከነጨርቁ ፣ ሸሚዝ፣ የተለያዩ 6000 ቴትረን ጨርቆች፣ የተለያዩ ቀለም ያላቸው ካኪ ብትን ጨርቆች፣ የሴቶች ቆዳ ጫማ፣ የወንዶች ቆዳ ጫማ፣ ሲፍቲ ሹዝ/ጫማ/፣ ፕላስቲክ ቦት ጫማ፣ የቆዳ ሽርጥ፣ የአይን መከላከያ ጉግል እና ቱታ ላይ የድርጅቱን አርማ የማተም አገልግሎት፣ የቤርጋሞድ ክር /Nylon thread/፣ ፕላስቲክ ጓንት፣
- የተለያየ የቧንቧ እቃዎች፣ የውሃ ፓምፕ፣ Submersible Pump ፣
- የሠራተኞች መዝናኛ ክበብ አገልግሎት፣
- የተባይ ማጥፊያ (Pest Control/
- የእሳት አደጋ መሙላት አገልግሎት፣
- የበሬ ላይ ቁጥር መፃፊያ ቀለም እና ሌሎች፣
- የተለያዩ መጠን ያላቸው ብረታ ብረቶች እና ሌሎች
- የተለያዩ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣
ማንኛውም ተጫራች፡
- በዘርፉ ወይም በተመሳሳይ ህጋዊና የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያለው፣ የተእታ ተመዝጋቢ የሆነ እና የቲን ሰርተፍኬት ያለው ለእያንዳንዱ የጨረታ ዓይነት የማይመለስ ብር 50 /ሃምሳ በመክፈል በስራ ሰዓት ከግዥና ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 30 ዝርዝር መረጃ የያዘውን የጨረታ ሠነድ ማግኘት ይችላል።
- የጨረታ ማስከበሪያ ቢድቦንድ/ ለሚጫረትበትየጠቅላላ ዋጋውን 2% በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርበታል።
- የጨረታ ሰነዶችና ከጨረታው ጋር ተያያዥ የሆኑ ሠነዶችን በፖስታ በማሸግ ከጨረታ መዝጊያው ሰዓት በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለበት፡
- ጨረታው መስከረም 5 ቀን 2013 ዓም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 የሁሉምተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ውስጥ ይከፈታል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011 4 65 22 94 /011 4 66 75 01 መጠየቅ ይቻላል፡፡
የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት